የግብፁ ህዝባዊ አብዮት አምስተኛ አመት | አፍሪቃ | DW | 26.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የግብፁ ህዝባዊ አብዮት አምስተኛ አመት

የግብፁ ህዝባዊ አብዮት አምስተኛ አመት በተከበረበት በትናንትናው እለት የአብዮቱ ማዕከል በነበረው በታህሪር አደባባይ በአል ሲሲ ላይ ሊነሳ የሚችል ተቃውሞን ለመከላከል ጭንብል ያጠለቁ በርካታ ፖሊሶች ተሰማርተው ነበር ።ተቃዋሚዎች ሊሰባሰቡባቸው ይችላሉ ተብለው የተገመቱ ቡና ቤቶችና ሌሎችም ማዕከላት በፖሊስ ተወረው እንዲዘጉ ተደርጓል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:02

የግብፁ ህዝባዊ አብዮት አምስተኛ አመት


የግብፁ ህዝባዊ አብዮት ከተካሄደ ከአምስት አመት በኋላ የግብፅ ዲሞክራሲ ወደፊት ሳይሆን ወደ ኋላ እየተጓዘ መሆኑን ተችዎች ይናገራሉ ።ከሁለት አመት ተኩል በፊት ሥልጣን የያዙትን የግብጹን ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል ሲሲንም ሃገሪቱን ወደ ቀድሞው ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ አምባገነን አገዛዝ በመመለስ የዛሬ አምስት አመት አደባባይ የወጣውን ህዝብ ተስፋ በማጨለም ይወቅሷቸዋል ። የግብፁ ህዝባዊ አብዮት አምስተኛ አመት በተከበረበት በትናንትናው እለት የአብዮቱ ማዕከል በነበረው በታህሪር አደባባይ በአል ሲሲ ላይ ሊነሳ የሚችል ተቃውሞን ለመከላከል ጭንብል ያጠለቁ በርካታ ፖሊሶች ተሰማርተው ነበር ።ተቃዋሚዎች ሊሰባሰቡባቸው ይችላሉ ተብለው የተገመቱ ቡና ቤቶችና ሌሎችም ማዕከላት በፖሊስ ተወረው እንዲዘጉ ተደርጓል ።ቀጣዩ የዶዶቼቬለው የዮርገን ሽትራይክ ዘገባ የዛሬ አምስት አመቱን ህዝባዊ አብዮት አነሳስና አካሄድ መለስ ብሎ ያስቃኘናል ።ይልማ ኃይለ ሚካኤል አጠናቅሮታል ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic