የግራዚያኒ የተቃዉሞ ሰልፍና እስራት | ኢትዮጵያ | DW | 18.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የግራዚያኒ የተቃዉሞ ሰልፍና እስራት

ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መሰጠት የአባቶቻችንን መስዋዕትነት ማራከስ ነዉ በሚል መሪ ሃሳብ ትናንት አዲስ አበባ ላይ የተቃዉሞ ሰልፍ ለማካሄድ ስድስት ኪሎ ከተሰበሰቡት መካከል ፖሊስ ማሰሩን ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር የላከል ዘገባ ያስረዳል።

ዶክተር ያቆብ ኃይለ ማርያም፤ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትና የጋዜጣ አምደኛ ታዲዮስ ታንቱን ጨምሮ የታሳሪዎቹ ቁጥር ከሰልፉ ማግስት ቅስቀሳ አካሂዳችኋል ተብለዉ ከታሰሩ ስምንት ወጣቶችን ጋ 34 መድረሱም ተገልጿል። ዘግይቶ በደረሰን ዜና መሠረት ደግሞ ታሳሪዎቹ ከአንዱ በስተቀር በዋስ መለቀቃቸዉን ያመለክታል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic