የግራዚያኒ ሐዉልት ያስከተለዉ ዉዝግብ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 11.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የግራዚያኒ ሐዉልት ያስከተለዉ ዉዝግብ

በአንድ ጀንበር በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን ኢትዮጵያዉያንን ላስጨፈጨፈዉ የፋሺስት ጣሊያን የጦር ጀነራል ሩዶልፎ ግራዚያኒ በተወለደበት ከተማ የተሠራለት የመታሰቢያ ሐዉልት ዉዝግብ ካስነሳ ሰንብቷል። ለጀነራሉ ሐዉልት መቆም የለበትም ባዮቹ በእሱ ትዕዛዝ ወገኖቻቸዉ ያለቁባቸዉ ኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆኑ ጣልያንያዉያንም እንደሚቃወሙት ነዉ የሚነገረዉ።  

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:09

ግራዚያኒን ወደ ኢትዮጵያ ያዘመተዉ ቤኒቶ ሙሶሎኒ፤

ሐዉልቱ እንዲገነባ ያደረጉት የላዚዮ ከተማ ከንቲባ እና ተባባሪዎቻቸዉም ክስ ቀርቦባቸዋል። ሐዉልቱ እንዲፈርስ ጥያቄ የሚያቀርብ የኢትዮጵያዉያን ጥምረትም ጉዳዩን በመከታተል ላይ መሆኑን ይገልጻል። ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለመጪዉ ያመት ኅዳር ወር ቀጥሮታል። በጣሊያኗ አፊሌ ከተማ ተወልዶ ፋሺት ጣሊያን ኢትዮጵያን ስትወርር የጦር አዛዥ በመሆን ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ የወረራዉ ዘመን እስኪያበቃ እዚያዉ መቆየቱም ይታወሳል። ዝግጅቱን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ተኽለዝጊ ገብረ ኢየሱስ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic