የግሪክ ፖለቲካዊ ቀዉስና አዉሮጳ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 10.05.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የግሪክ ፖለቲካዊ ቀዉስና አዉሮጳ

የሰወስተኝነቱን ደረጃ የያዘዉ የሶሻሊስቱ ፓርቲ ዛሬ ሌላ ሙከራ ጀምሯል።ሙከራዉ ካልተሳካ ካንድ ወር በሕዋላ ሌላ ምርጫ ይደረጋል።የግሪክና የፈረንሳይ ምርጫ በአዉሮጳ የቁጠባ መርሕ ላይ ያስከተለዉ ተፅዕኖ ግን አሁንም እያነጋገረ ነዉ።

Greece's Socialist PASOK leader Evangelos Venizelos delivers a statement after his meeting with Greece's conservative leader of New Democracy Antonis Samaras at the Greek Parliament in Athens, Monday, May 7, 2012. Greece faces weeks of political turmoil that could scupper its financial bailout after voters angry at crippling income cuts punished mainstream politicians, let a far-right extremist group into Parliament and gave no party enough votes to govern alone. (Foto:Petros Giannakouris/AP/dapd)

የሶሻሊስቱ ፓርቲ መሪ-ኢቫንጌሎስ ቬኒዜሎስ

ባለፈዉ ዕሁድ ግሪክ ዉስጥ በተደረገዉ ምርጫ ከፍተኛዉን ድምፅ ያገኙት ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች መንግሥት ለመመሥረት ያደረጉት ጥረት ከሸፈ።የመጀመሪያዉን ደረጃ የያዘዉ አዲሱ ዲሞክራሲ የተሰኘዉ የመሐል-ቀኝ ፓርቲና ሁለተኛዉ፥ ሲረዛ የተሰኘዉ የግራ ፅንፈኛዉ ፓርቲ መንግሥት ለመመሥረት በየተራ ያደረጉት ሙከራ ያለዉጤት በማብቃቱ፥ የሰወስተኝነቱን ደረጃ የያዘዉ የሶሻሊስቱ ፓርቲ ዛሬ ሌላ ሙከራ ጀምሯል።ሙከራዉ ካልተሳካ ካንድ ወር በሕዋላ ሌላ ምርጫ ይደረጋል።የግሪክና የፈረንሳይ ምርጫ በአዉሮጳ የቁጠባ መርሕ ላይ ያስከተለዉ ተፅዕኖ ግን አሁንም እያነጋገረ ነዉ።ገበያዉ ንጉሴ ከብራስልስ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic