የግሪክ ጠ/ሚ የበርሊን ጉብኝት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 23.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የግሪክ ጠ/ሚ የበርሊን ጉብኝት

የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕራስ ከጥቂት ሰዓታቶች በፊት ጀርመን መዲና በርሊን ላይ ይፋዊ ጉብኝታቸዉን ጀምረዋል።

የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ለአዲሱ የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር በደማቅ ወታደራዊ አጀብ ነዉ በጽሕፈት ቤታቸዉ አቀባበል ያደረጉላቸዉ። ሲፕራስ የሃገራቸዉ የቁጠባ መረሃ-ግብር የመጀመርያ ረቂቅ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። እንዲያም ሆኖ የተባለዉን ቁጠባ ተግባራዊ ለማድረግ ከኅብረቱ ተጨማሪ የገንዘብ ርዳታ እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል።

ባለፈዉ ሳምንት የአዉሮጳዉ ሕብረት ሃገራት ተወካዮች ብራስልስ ላይ ባካሄዱት ስብሰባ ግሪክ ከሕብረቱ የገንዘብ ርዳታን ከፈለገች መጀመርያ ሕብረቱ በጠየቃት መሠረት የራስዋን የቁጠባ መረሐ-ግብር ማቅረብ እንዳለባት ዳግም ተናግረዋል። የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትርን የበርሊን ጉብኝትን በተመለከተ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤልን አነጋግሬዉ ነበር።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ

ሸዋዩ ለገሰ

Audios and videos on the topic