የግሪክ ዕዳ ቀዉሰና አዉሮጳ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 07.02.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የግሪክ ዕዳ ቀዉሰና አዉሮጳ

የአቴንሱ መንግስት ያለዉን በጀት ወጭና ገቢ እንዲያስተካክል በአለም አቀፍ ደረጃ የሚደርስበት ግፊት እየጥነከረ መጥቶአል፣ በሌላ በኩል ግሪክ ከዕዳ ለመላቀቅ የጀመረችዉን የቁጠባ ታህድሶን በመንቀፍ ዛሪ ህዝብ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ አድርጎአል። የግሪክ የቁጠባ ዕቅድ እና ሂደቱ

የአቴንሱ መንግስት ያለዉን በጀት ወጭና ገቢ እንዲያስተካክል በአለም አቀፍ ደረጃ የሚደርስበት ግፊት እየጥነከረ መጥቶአል፣ በሌላ በኩል ግሪክ ከዕዳ ለመላቀቅ የጀመረችዉን የቁጠባ ታህድሶን በመንቀፍ ዛሪ ህዝብ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ አድርጎአል። የግሪክ መንግስት በአገሪቱ የደረሰዉን የገንዘብ ኪሳራ እንዲያቃልል አበዳሪ ወገኖች ባስቀመጡት የቁጠባ ዕቅድ መሠረት፣ የመንግስት የሰራተኞችን ለመቀነስ የተነደፈዉን መረሃ-ግብር ሥራ ላይ ለማዋል ግሪክ የጀመረችዉ ሽሽት የተሳካላት አይመስልም። በግሪክ  የመንግስት መስሪያ ቤቶች የታህድሶ ለዉጥን አስተዳደር ሚኒስትር ዲሚትሪስ ሪፓስ ትናንት ይፋ እንደደረጉት የግሪኩ ጥምር መንግስት በያዝነዉ የጎርጎሮሳዉያኑ አመት ብቻ 15.000 ያህል የስራ ቦታዎችን ይሰርዛል። የቴንሱ መንግስት አገሪቱ ከገባችበት ቀዉስ እንድትወጣ የአዉሮጳዉ ኮሚሲዮን ያስቀመጠለትን የቁጠባ መረሃ-ግብር ተግባራዊ ለማድረግ ገና ዉጣ ዉረድ ላይ ነዉ።የኮሚሲዮኑን የቁጠባ እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የግሪኩ ጠቅላይ ሚንስትር ፓፓዲሞስ ደጋፊ ፓርቲዎችን ዛሪ ሊያነጋግሩ በዝግጅት ላይ መሆናቸዉ ሲታወቅ-የአዉሮጳዉ ህብረት ኮሚሽን ግን ትግስቱ እንደተሟጠጠ ተነግሮአል። ለግሪክ ዕዳ ቀዉስ ከፍተኛ የገንዘብ ድጎማ የሚያደርጉት ፈረንሳይ እና ጀርመን ግሪክ ቁጠባ እንድታደርግ ጫና እያደረጉ ነዉ። የዕለቱ ዝግጅታችን የግሪኩ ቀዉስ እና የአዉሮጳ ህብረት በግሪክ ላይ የሚደርገዉን ግፊት ይቃኛል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

 • ቀን 07.02.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/13yqF

ተዛማጅ ዘገባዎች

 • ቀን 07.02.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/13yqF