የግሪክ ዉሳኔና የአዉሮጳ ፈተና | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 06.07.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የግሪክ ዉሳኔና የአዉሮጳ ፈተና

ግሪክ የደረሰባትን የኤኮኖሚ ቀዉስ ለመታደግ እንዲሁም ተጨማሪ ብድር ለማግኘት አበዳሪዎችዋ ያስቀመጥዋቸዉን ቅድመ ግዴታዎች ትናንት ባካሄደችዉ በሕዝበ ዉሳኔ ላለመቀበል መወሰንዋ ይታወቃል።

የግሪኩ የኤኮኖሚ ሚኒስትር ቫሩፋኪስ ዛሬ በገዛ ፈቃዳቸዉ ከስልጣን ወርደዋል። በግሪክ ሕዝበ ዉሳኔ ላይ የጀርመን ፖለቲከኞች ምን እያሉ ይሆን? የአዉሮጳ ማኅበረሰብ እንዲሁም የብረስልስ ፖለቲከኞች በዚሁ ጉዳይ ላይ ምን አስተያየት እየሰጡ ነዉ? የይሮ ተጠቃሚ ሃገራቱ ይህን የደረሰባቸዉን ችግር እንዴት ነዉ ለመፍታት የሚያስቡት የተሰማ ነገር ይኖር ይሆን? እንደሚታወቀዉ ጀርመን ከሸርፉ ተጠቃሚ አባል ሃገራት መካከል ብዙዉን የብድር ገንዘብ ሰጭ ናት። በርሊንስ ይህን ችግር እንዴት ለመፍታት ነዉ የምታስበዉ? የሸርፉ ተጠቃሚ አባል ሃገራት በግሪክ ዉሳኔ የተለያየ አቋም ይዘዉ የተለያየ ዉሳኔ ላይ ይደርሱ ይሆን ? የግሪክ እንቢኝ ዉሳኔ የሚያመጣዉ ተፅኖ ምን ይሆን? እንዲሁም ግሪክስ በዚህ ርምጃዋ ምን ይከተላት ይሆን? የሚሉትን ጥያቄዎች ፤በበርሊን እንዲሁም በአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን መቀመጫ ብረስልስ ከሚገኙት ወኪላቾቻችን ጋር በስልክ የቀጥታ ቃለ ምልልስ አድርገናል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic