የግሪክ እና የአበዳሪዎቿ ውዝግብ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 29.06.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የግሪክ እና የአበዳሪዎቿ ውዝግብ

ግሪክ በአሳሳቢ የፊናንስ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። የግሪክ ጠቅላይ ሚንስትር አሌክሲስ ሲፕራስ የሀገራቸው አበዳሪዎች ለግሪክ አዲስ ብድር ይሰጡ ዘንድ ባቀረቡት ጠንካራ የቁጠባ መርሀግብር ላይ የግሪክ ዜጎች ድምፃቸውን አንዲሰጡ ለፊታችን እሁድ ውሳኔ ሕዝብ ጠርተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:25
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:25 ደቂቃ

የግሪክ እና የአበዳሪዎቿ ውዝግብ

ግሪክ ያለባትን እዳ በተመለከተ ከአዉሮጳዉ ሕብረት ጋር የጀመረች ዉይይት ስኬት ከራቀዉ ወዲህ ግሪክ መንግሥት ሕዝቡ ባንክ ዉስጥ ያስቀመጠዉ ገንዘብ ደሕንነቱ የተጠበቀ ነዉ፤ ምንም ፍርሃት እና ሥጋት እንዳይኖረዉ ሲል ጥሪዉን አስተላለፈ። ከዚህ ጋር ተያይዞ የገንዘብ ዝዉዉር በመጠኑ እንደሚሆንም አስታዉቋል። እስከ ፊታችን ሰኔ 29 በግሪክ የሚገኙ ባንኮች ሁሉ ተዘግተዉ እንደሞቆዩም ተመልክቶአል። ባንኮች ዝግ ሆነዉ የሚቆዩት የፊታችን እሁድ ገንዘብ አበዳሪዎች ለግሪክ ያስቀመጡትን የተኃድሶ መረሃ-ግብር የግሪክ ዜጎች ሕዝበ ዉሳኔ እስከሚሰጡበት ድረስ መሆኑ ነዉ የተነገረዉ። አንድ የግሪክ ዜጋ በቀን ከባንክ ማዉጣት የሚችለዉ ደግሞ ስድሳ ይሮ ብቻ መሆኑም ተገልጿል። በሌላ በኩል የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ህዝቡ የተሃድሶዉን መረሃግብር እንዳይቀበል ጥሪ ማስተላለፋቸዉ ነዉ የተመለከተዉ። ይህን ተከትሎ፤ የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር በግሪክ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ትችትን ሰንዝረዋል። እንደ ሽታይን ማየር ግሪክ ያለባትን እዳ ለመመለስ የጀመረችዉ ድርድር ስኬታማ ያልሆነዉ በግሪክ መንግሥት በተለይ በጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕራስ አቋም መሆኑን ተናግረዋል፤


«ባለፉት ቀናት ከግሪክ መንግሥት በተለይም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል በማየዉ ሁኔታ እጅግ ተገርሜያለሁ። ሙከራዉ በእዉነቱ ጊዜ ገዳይ እና ከአዉሮጳዉ ሕብረት ፍላጎት በተቃራኒዉ የቆመ ነዉ። እንደኔ እምነት በሁሉም ሁኔታና መንገድ ግሪክ የጋራ ሸርፍ ተጠቃሚ አባል ሁና እንድትዘልቅ ፍላጎታችን መሆኑን አሳይተናል። ከድርድሩ መዉጣት የግሪክ ዉሳኔ ነዉ፤ ሆኖም ለሕዝበ ዉሳኔ እንዲቀርብና ሕዝቡም አሉታዊ መልስ እንዲሰጥ መንግሥት መምከሩ ግን ያልተለመደ አካሄድ ነዉ።»
ወቅታዊዉን የግሪክ የኤኮኖሚ ቀዉስን በተመለከተ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ዛሬ ሰኞ በጀርመን ምክር ቤት የሚገኙትን ሁሉንም የፓርቲ ተወካዮች ሰብስበዉ አነጋግረዋል።

የሀገራቸው ባንኮች ከዛሬ ጀምረው ለአንድ ሳምንት እንዲዘጉም ወስነዋል። ጠቅላይ ሚንስት እነዚህን ሀሳቦች ያቀረቡት በሀገራቸው እና በአበዳሪዎችዋ መካከል ለግሪክ የብድር ቀውስ መፍትሔ ለመሻት የተካሄደው ድርድር ባለፈው ቅዳሜ ካለውጤት ከተበተነ በኋላ ነው። ግሪክ ስለምትገኝበት ቀውስ ምክክሩ የቀጠለባቸው ብራስልስ እና በርሊን ጉዳዩን እንዴት እያዩት ነው?

ገበያው ንጉሤ /ይልማ ኃይለ ሚካኤል

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic