የግሪክ ምክር ቤት በቁጠባ እቅዱ መስማማቱ | ኤኮኖሚ | DW | 17.07.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የግሪክ ምክር ቤት በቁጠባ እቅዱ መስማማቱ

የግሪክ ምክር ቤት ተጨማሪ ብድር ለማግኘት ከአዉሮጳ ኅብረት የቀረበለትን ጠንካራ የተባለዉን ቅድመ ግዴታ በአብላጫ ድምጽ ዛሬ መቀበሉን አሳዉቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:52
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:52 ደቂቃ

የግሪክ ምክር ቤት በቁጠባ እቅዱ መስማማቱ

አቴንስ የበፊቱ እዳዋ ወይ እንዲሰረዝላት አለያም የመክፈያ ሁኔታዎች እንዲመቻቹላት ስትወተውት ብትቆይም ያኛዉ እልባት ሳያገኝ ነዉ በድጋሚ ለጠየቀችዉ የ86 ቢሊዮን ዩሮ ብድር በቅድመ ግዴታነት የቁጠባ መርሃግብሮችን ተግባራዊ እንድታደርግ የተስማማችዉ። የግሪክ ምክር ቤት ግን እዚህ ዉሳኔ ላይ ለመድረስ በዉስጡ ከፍተኛ ክፍፍል ተፈጥሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕራስም ከፍተኛዉ ተቃዉሞ የገጠማቸዉ ከግራዉ የራሳቸዉ ፓርቲ ከሲሪዛ ነዉ። አብዛኞቹ የሲሪዛ አባላት ዉሳኔዉን ግሪክን ያዋረደ ነዉ ሲሉ ተቃዉመዋል። የዚሁ ፓርቲ አባል የሆኑት የግሪክ የአገር ዉስጥ ሚኒስትርም በቅርቡ ማለትም በፊታችን መስከረም አዲስ ምርጫ ሊካሄድ እንደሚችል ጠቁመዋል። ስለግሪክ ምክር ቤት ዉሳኔና በቀጣይ ስለሚጠበቀዉ ርምጃ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለዉ የብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሩዋለሁ።

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic