የግሪኩ ጠ/ሚ በድንገት ስልጣን መልቀቅና በግሪክ የምርጫ ዝግጅት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 21.08.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የግሪኩ ጠ/ሚ በድንገት ስልጣን መልቀቅና በግሪክ የምርጫ ዝግጅት

የግሪክ ጠ/ሚ አሌክሲስ ሲፕራስ በፈቃዳቸዉ ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣናቸዉ በመነሳት ምርጫ እንዲካሄድ ጠይቀዋል።ጠ/ሚ ሲፕራስ የሥራ መልቀቂያቸዉን ትናንት ነዉ ያስገቡት።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:40
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:40 ደቂቃ

የግሪኩ ጠ/ሚ በድንገት ስልጣን መልቀቅና በግሪክ የምርጫ ዝግጅትለግሪኩ ፕሬዚዳንት ፕሮኮፒስ ፓቭሎፖሎስ ያቀረቡት ከአዉሮጳ ኮሚሽንና ሌሎች አበዳሪ ሀገሮችና ድርጅቶች ጋር ለረጅም ጊዜ

ሲደራደሩበት የነበረዉ ሶስተኛዉ የ 86 ቢሊዮን ይሮ የብድርና ርዳታ ፕሮግራም ፀድቆ የመጀመርያዉ ክፍያ 13 ቢሊዮን ይሮ ለመንግሥታቸዉ በተላለፈ ማግሥት መሆኑ ነዉ። ጠ/ሚ ሲፕራስ ከስድስት ወራት በፊት የግራ ኃይሎች ጥምረት ወደ ሥልጣን መንበር ሲወጡ አበዳሪ ድርጅቶች በተለይም የይሮ ተጠቃሚ ሀገሮች በግሪክ ላይ የጣሉትን አስገዳጅ የቁጠባና የኤኮኖሚ ፖሊሲ በመቃወም ሀገራቸዉን «ኔዎ ሊበራልስ» ከሚሉዋቸዉ አበዳሪዎች ጥገኝነት ነጻ እንደሚያወጡ ቃል ገብተው ነበር። ዝርዝሩን የብራስልሱ ወኪላችን ልኮልናል።


ገበያዉ ንጉሴ


አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic