የግልገል ጊቤ ሰራተኞች በመኪና አደጋ ሞቱ | ኢትዮጵያ | DW | 29.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የግልገል ጊቤ ሰራተኞች በመኪና አደጋ ሞቱ

ወደ ሥራ ቦታቸው በማምራት ላይ የነበሩ የግልገል ጊቤ ሁለት የኃይል ማመንጫ ሰራተኞችን የጫነ ተሽከርካሪ ተገልብጦ 13 ሰዎች ሲሞቱ 10 ሰዎች ቆሰሉ።

የሰራተኞች ማጓጓዣው 23 ሰዎችን ጭኖ ነበር። የአደጋው ምክንያት እየተጣራ መሆኑን የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የኮምዩንኬሽን ዳይሬክቶሬት ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ አስቴር ተክሌ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። «  ከትራፊክ አደጋ ነው እኛም መረጃው የደረሰን። መኪናው ተገልብጦ ይመስለኛል። የተጣራ ነገር የለም። የሰራተኞች ሰርቪስ ነበር። ሰራተኞች ሞተዋል። ወደ ስራ ሲሄዱ የነበሩ ናቸው። »
ከሰባት ዓመት በፊት የተመረቀው የግልገል ጊቤ ሁለት የኃይል ማመንጫ በኦሮሚያ ክልል ከጅማ 80 ኪሜ በስተ ምስራቅ ርቀት ላይ ይገኛል። የኃይል ምንጩ የኦሞ ወንዝ ነው።

ልደት አበበ

እሸቴ በቀለ