የጋዜጣ ኅትመት ዋጋ መናር፣ | ኢትዮጵያ | DW | 04.04.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጋዜጣ ኅትመት ዋጋ መናር፣

በኢትዮጵያ የጋዜጣ ኅትመት ዋጋ በአንድ ጊዜ፤ የ 50% የማሳተሚያ ዋጋ ጭማሪ ተደርጎበታል። የ 50% የዋጋ ጭማሪ ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ፣ ለማሳተም ከአቅማችን በላይ ሆኗል በማለት፤ ጉዳዩን በባለሙያ አስጠንተን፣

default

አማራጭ ሐሳብ እስከምናቀርብ፤ የ 3 ወር ጊዜ ይሰጠን በማለት ለብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጥያቄ ያቀረቡት  የጋዜጣ አሳታሚዎች፤ ጥዮያቄአቸው ውድቅ መሆኑን፤ ዘጋቢአችን፤ ታደሰ እንግዳው የላከልን ዘገባ ያስረዳል። የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በበኩሉ፤ ጥያቄውን መመለስ የአንድ ሰዓት ሥራ ሆኖ ሳለ ለ 3 ወር መጠበቅ አያስፈልገኝም

የሚል ምላሽ የሰጣቸው   አሳታሚዎች ተሰባስበው በመምከር ፣ ወጥ-አቋም ለመያዝ እየጣሩ ይገኛሉ።

ታደሰ እንግዳው

ሒሩት መለሰ