የጋዜጣ መዘጋትና የዘጋቢዎች መሰደድ | ኢትዮጵያ | DW | 07.12.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጋዜጣ መዘጋትና የዘጋቢዎች መሰደድ

ዓለም ዓቀፍ ድንበር አያግዴ ድርጅት (ኤር ኤስ ኤፍ) በኢትዮጵያ የፕረስ ነፃነት ይዞታ እንደሚያሳስበዉ በመጥቀስ መግለጫ አዉጥቷል። በአዲስ ነገር ጋዜጠኞች ላይ የሚደረገዉ ወከባ አላበቃም ነዉ የሚለዉ። ሸዋዬ ለገሠ፣

default

በደረሰብን ጫና ሙያዊ ተግባራችንን ማከናወን አልቻልንም ሳምንታዊ ጋዜጣችንም ከመታተም አቁማለች የሚሉት የአዲስ ነገር ጋዜና አዘጋጆችና ዘጋቢዎች ከአገር ለመዉጣት መገደዳቸዉን አስረድተዋል። የሚገኙበትን ለደህንነታችን ሲባል እትግለፁ ያሉት የጋዜጣዉ ዘጋቢዎች ዋና አዘጋጆቹ ከአገር ቢወጡም ማስፈራሪያዉ ባለመቆሙ እኛም ለመዉጣት ተገደናል ነዉ ያሉት። ዘሪሁን ተስፋዬ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአዲስ ነገር ጋዜጣ የኤኮኖሚ ዘገባና ትንታኔ ሲያቀርብ መቆየቱን ገልፆ ምን ከዚህ ዉሳኔ እንዲደርስ እንዳደረገዉ ላቀረብንለት ጥያቄ ሲመልስ፤

ድምፅ

ባልደረባዉ አብርሃም በጊዜዉ ባለፈዉ ዓመት ሐምሌ ሁለት ቀን ከሰራዉ ዘገባ ጋ በተገናኘ ማንነታቸዉ ባልታወቀ ሰዎች እንደተደበደበ ገልፆ ይህ ሁሉ እየሆነ ሙያዊ ግዴታዉን ለመወጣት ሲጥር እንደቆየ ነዉ ያስረዳዉ፤

ድምፅ

የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆች ለክስ የሚያዉሉ በተለዩ ጊዜያት ቀረቡብን ያሏቿዉ ዘገባዎችን ተንተርሰዉ ለመሰደድ መብቃታቸዉ ጉዳዩ እንዳሉት አይደለም የሚል ወገን ቢኖር ምን ምላሽ አላችሁ ለሚለዉ ጋዜጠና አብረሃን ሲናግር፤

ጋዜጠኞቹ ደረሰብን ያሉትን ጫናና ወከባ አስጊና አሳሳቢ ነዉ ሲል መቀመጫዉን ፓሪስ ያደረገዉ ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች መግለጫ አዉጥቷል። የድርጅቱ ባልደረባ ቪንሰንት ብሮሴል

«ይህ ሳምንታዊ ጋዜጣ ከመንግስት በደረሰበት በርካታ ጫና ህትመቱን ለማቋረጥ መገደዱና በተመሳሳይ ከባለስልጣናት በተፈፀመባቸዉ ፖለቲካዊ ተፅዕኖና ወከባ የጋዜጣዉ አርታኢዎች ከአገር ለመዉጣት መገደዳቸዉ የጉዳዩን አሳሳቢነትና አስፈሪነት ለመረዳት አስችሎናል። ጉዳዩ እኛን አሳስቦናል። ምክንያቱም በግንቦት ምርጫ ይካሄዳል። መንግስት ለፕረሱና የሰላ ሂስ ለሚሰነዝሩ ተቃዋሚ ድምፆች ሳይቀር የተሻለ ሁኔታ ይፈጥራል ተብለን ነበር። ግን እንደአዲስ ነገር ያለዉ ሳምንታዊ ጋዜጣ ከሚባሉት ተፅዕኖዎች ነፃ ሆኖ በአገሪቱ መታተም ካልቻለ ሊያሳስበን የሚገባ ትልቅ ጉዳይ ይሆናል። ያም በመጪዉ የግንቦት ወር የሚካሄደዉ ምርጫ ነፃና ፍትሃዊ ነዉ የሚለዉን ጥያቄ ላይ ይጥለዋል።»

በየዓመቱ የየአገራቱን የፕረስ ነጻነት ይዞታ በመከታተል ደረጃ እየሰጠ መረጃዎችን ይፋ የሚያደርገዉ ይህ የመገናኛ ብዙሃንና የጋዜጠኞች መብት እንዲከበር የሚጥረዉ ድርጅት እንደሚለዉ ከዚህ ቀደም የአገሪቱ የፕረስ ነፃነት ይዞታ እንደሚሻሻል ከባለስልጣናቱ ቃል ተገብቶለት ነበር፤

«ባለፉት ጊዜያት በተለይም ደግሞ በ1997ዓ,ም ፕረሱ ከፍተኛ ወከባና ጫና ደርሶበታል። ሆኖም ባለፈዉ ዓመት በኢትዮጵያ በነበረን ተልዕኮ ሚኒስትሩን ሁሉ አግኝተን ቃልም ገብተዉልን ነበር። ርግጥ ነዉ የፕረስ ነጻነት መንግስት በሚገባዉ ቃል ብቻ የሚመዘን አይደለም። አሁንም ከምርጫዉ በፊት ምን ሊሆን ይችላል በሚል በቅርበት እየተከታተልን ነዉ። ለዚህም ነዉ ይህን ጉዳይ ይዘን የሁኔታዉን አሳሳቢነት የገለጽነዉ።»

ቪንሰንት ብሮሴል ጨምረዉም ለመንግስት የዚህን ጋዜጣ መዘጋትን ጋዜጠኞቹ ደረሰብን ባሉት ጫና ከአገር ለመዉጣት መገደዳቸዉን አስመልክተዉ ደብዳቤ ፅፈዉ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸዉን ገልፀዋል። የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጅና ዘጋቢዎች ደረሰብን ያሉትን በመያዝ ከመንግስት ወገን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነዉ ጥረት ለጊዜዉ አልተሳካም።

ሸዋዬ ለገሠ/ቨንሶ ብሮሰ (ኤር ኤስ ኤፍ)

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ