የጋዜጠኞች ክስና እስራት በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 09.02.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጋዜጠኞች ክስና እስራት በኢትዮጵያ

ጋዜጠኛ ኢዘዲን መሐመድ መታሰሩን አለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች አብጥበቀዉ ተቃዉመዉታል። ኢዘዲን ይሠራበት የነበረዉ መፅሔትና ጋዜጣ ኃላፊ እንደሚሉት ጋዜጠኛዉ ዳግም ክስ የተመሠረተበት ገና ታትሞ ባልተሰራጨ መፅሔት ላይ አግባብ ያልሆነ ርዕሥ ሊወጣ ነበር በሚል ነዉ

default

የፕሬስ ነፃነት

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት ከዚሕ ቀደም የተከሰሱ የአራት የጋዜጣና የመፅሔት አሳታሚ ድርጅቶችን ጉዳይ ከአንድ ወር በኋላ የመጨረሻ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ከዚሕ ቀደም የአንድ አመት እሥራት የተበየነበት የአል-ቅዱስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ኢዘዲን መሐመድ ደግሞ ሌላ ክስ ተመስርቶበታል። ጋዜጠኛ ኢዘዲን መሐመድ መታሰሩን አለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች አብጥበቀዉ ተቃዉመዉታል። ኢዘደኒን ይሠራበት የነበረዉ መፅሔትና ጋዜጣ ኃላፊ እንደሚሉት ጋዜጠኛዉ ዳግም ክስ የተመሠረተበት ገና ታትሞ ባልተሰራጨ መፅሔት ላይ አግባብ ያልሆነ ርዕሥ ሊወጣ ነበር በሚል ነዉ።

ታደሰ እንግዳዉ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ