የጋዜጠኛ ኤልያስና የፖለቲከኛ አቶ ዳንኤል ጉዳይ | ኢትዮጵያ | DW | 12.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጋዜጠኛ ኤልያስና የፖለቲከኛ አቶ ዳንኤል ጉዳይ

በእስር የሚገኙት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩና የተቃዋሚው የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ፍትሕ ፓርቲ የአመራር አባል አቶ ዳንኤል ሽበሺ ሰሞኑን ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እንዲመለሱ ተደረገ። የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታሳሪዎቹን ወደማዕከላዊ ቢልካቸውም፣ ማዕከላዊ ግለሰቦቹን ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስካስተላለፏቸው ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:43

በጋዜጠኛ ኤልያስና በቀድሞ የአንድነት አባል አቶ ዳንኤል ላይ ክስ የሚመሰርት አካል ጠፋ።

ከታሰሩ አምስት ወራት የሆናቸው ጋዜጠኛ ኤልያስ እና አቶ ዳንኤል እንደገና መጀመሪያ ወደነበሩበት ፖሊስ ጣቢያ እንዲመለሱ የተደረገው ክስ የሚመሰርትባቸው አካል በመጥፋቱ መሆኑ ተሰምቷል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለስ

Audios and videos on the topic