የጋዜጠኛ ተመስገን መታሠር | ኢትዮጵያ | DW | 14.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጋዜጠኛ ተመስገን መታሠር

የኢትዮጵያ መንግሥትን መርሕና አሠራር የሚተቹ መጣጥፎችን በማፃፍና በማሳተም የሚታወቀዉ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታሰረ።

ጋዜጠኛ ተመስገን ከዚሕ ቀደም በተዘጋዉ ፍትሕ በተሰኘዉ የግል ጋዜጣ ባሳተማቸዉ ፅሁፎቹ ተከሶ በፍርድ ቤት ሲሟጋት ነበር።ትንናት አዲስ አበባ ያስቻለዉ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛዉ በተከሰሰበት ወንጀል የጥፋተኛነት ዉሳኔ ሰጥቶ የመጨረሻዉ ብይን እስኪሰጥ ድረስ እስር ቤት እንዲቆይ ወስኖበታል።ፍርድ ቤቱ ብይኑን ለመስጠት ለፊታችን ጥቅምት 17 2007 ቀጠሮ ይዟል።ተመስገን ፍትሕ፤አዲስ ታይምስ፤ልዕለና እና ፋክት የተባሉ ጋዜጦችን መፅሔቶች ዋና አዘጋጅና ቋሚ አምደኛ ነበር። ነጋሽ መሐመድ የተመስገን የቅርብ የሥራ ባልደረባ ጋዜጠኛ ሐይለመስቀል በሸዋምየለህን በሥልክ አነጋግሮታል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic