የጋዜጠኛ ተመስገን ህክምና መከልከል | ኢትዮጵያ | DW | 20.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጋዜጠኛ ተመስገን ህክምና መከልከል

የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረዉ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእስር ቤት እያለ ለገጠመዉ የጤና መታወክ ህክምና እንዳያገኝ መከልከሉን ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተዉ CPJ በማመልከት ባለስልጣናት ታሳሪዉ ጋዜጠኛ ያለበትን ሁኔታ እንዲመለከቱ ጥሪ አቀረበ።

CPJ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የኢትዮጵያን ባለስልጣናትና በዋሽንግተን የኢትዮጵያን ኤምባሲ ለማነጋገር ሞክሮ እንዳልተሳካለት ይፋ ባደረገዉ መግለጫ በማመልከትም መንግሥትን በመተቸቱ ለእስር ተዳርጓል ያለዉን ጋዜጠኛ ተመስገን ላይ እየተፈፀመ ነዉ ያለዉ የመብት ጥሰት እንዲቆም ጠይቋል። የዋሽንግተን ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ጽህፈት ቤቱ ኒዉዮርክ የሚገኘዉን የCPJን አፍሪቃ ዘርፍ አስተባባሪን በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic