የጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉጌታ ሉሌ ዜና እረፍት | ኢትዮጵያ | DW | 05.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉጌታ ሉሌ ዜና እረፍት

አንጋፋዉ ጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉጌታ ሉሌ በ79ዓመቱ ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የቅርብ ጓደኞቹ የብዕር አርበኛ እያሉ የሚያወድሱት ጋዜጠኛ ሙሉጌታ በብዙዎች ዘንድ ፀጋዬ ገብረመድህን አርአያ በሚል የብዕር ስምም ይታወቃል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:23

የጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉጌታ ሉሌ ዜና እረፍት

በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ያገለገለዉ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ የደርግ ስርዓት ካከተመ በኋላ ከነበረበት የሥራ ኃላፊነት ሲሰናበት ከባልደረቦቹ ጋር ሆኖ የመሠረታት ጦቢያ መጽሔት ከፍተኛ ተነባቢነት ከነበራቸዉ የሀገሪቱ መጽሔቶች አንዷ ነበረች። ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በነፃ ጋዜጠኞች ማሕበር ምስረታ ከፍተኛ ሚና እንደነበረዉ የገለፀዉ በዉጪ የሚገኙ የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማኅበር፤ የጋዜጠኛዉ ስም ከመቃብር በላይ ዘላለማዊ ሆኖ ይኖራል ሲል በአጭር መግለጫዉ ገልጿል። ለወጣት ጋዜጠኞች አርአያ እንደነበር በመግለፅም ሕልፈተ ሕይወቱ ለነፃ ፕረስ ጋዜጠኞች እና ቤተሰቦች መሪር ሀዘን መሆኑንም መግለጫዉ አመልክቷል። ስለአንጋፋዉ ጋዜጠኛ እሱ የስደት ሕይወቱን በገፋባት ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ ሁለት በቅርብ የሚያዉቁትን ሰዎች ስቱዲዮ ከመግባቴ ቀደም ብዬ አነጋግሬያለሁ።

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic