የጋዛ ዕርዳታ መርከብ እንደገና ተያዘች | ዓለም | DW | 07.06.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የጋዛ ዕርዳታ መርከብ እንደገና ተያዘች

ቀደም ሲል ለጋዛ ሰርጥ ዕርዳታ የጫነችው ራሄል-ኮሪ የተሰኘች መርከብ ከነተሳፋሪዎቿ አቅጣጫዋን ካልቀየረች እንደሚይዛት አስጠንቅቆ ነበር።

default

የእሥራኤል ጦር በዛሬው ዕለት አንዲት የአየርላንድ የዕርዳታ መርከብን በዓለምአቀፍ የባሕር ክልል ውስጥ ከከበበ በኋላ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። አንድ ወታደራዊ ቃል-አቀባይ እንደገለጸው የመርከቧ ሠራተኞችና ተሳፋሪዎች ሙሉ በሙሉ በመተባበራቸው የደረሰ አንዳች ግጭት የለም። የእሥራኤል ጦር የእሥራኤል ሃይል ባለፈው ሣምንት መጀመሪያ ላይ ለጋዛ ፍልሥጤማውያን ዕርዳታ የጫነች የቱርክ መርከብን በመውረር ዘጠኝ ሰዎችን መግደሉም አይዘነጋም። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በድርጊቱ ያደረበትን ቁጣ በመግለጽ እሥራኤል በጋዛ ላይ የጣለችውን እገዳ በፍጥነት እንድታነሣ አስገንዝቦ ነበር። በአረቡ ዓለምም ድርጊቱን በመቃወም ትናንት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በየቦታው በአደባባይ በመሰለፍ ተመሳሳይ ጥሪ ሰንዝረዋል። እገዳው የተጣለው የፍልሥጤሙ እሥላማዊ እንቅስቃሴ ሐማስ ከሶሥት ዓመታት ገደማ በፊት ጋዛን ከተቆጣጠረ በኋላ ነበር።