የጋዛ ሠርጥ የመልሶ ግንባታ ጉባኤ | ዓለም | DW | 12.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የጋዛ ሠርጥ የመልሶ ግንባታ ጉባኤ

ለጋዛ ሰርጥ የመልሶ ግንባታ ካይሮ ውስጥ የተዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የለጋሾች ጉባኤ የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ከፈቱ። በጉባኤው ከ1.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ቃል መገባቱ ተነገረ።

ከ50 የሚበልጡ የሀገር ተወካዮች እና 20 የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሕዝብ ተጨናንቆ የሚኖርባቸው የፍልስጤም ይዞታዎችን መልሶ ለመገንባት በፋይናንስ መደገፍ የሚቻልበትን መንገድ ለማጤን ይመክራሉ ተብሏል። በእዚህ የጋዛ ሰርጥ የመልሶ ግንባታ ጉባኤ የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታን ማየር፣ የዩናይትድ ስቴትስ አቻቸው ጆን ኬሪ እና ሌሎችም ባለሥልጣናት ተገኝተዋል። በጉባኤው የተገኙት የዓለም አቀፍ ተወካዮች የመልሶ ግንባታው በፍልስጤም እና እስራኤል ዘላቂ የሆነ የሰላም መፍትኄ ላይ የተመረኮዘ እንደሆነ አስታውቀዋል። ጀርመን 63 ሚሊዮን ዶላር፣ ዩናይትድ ስቴትስ 212 ሚሊዮን ዶላር፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች 200 ሚሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም ቋታር 1 ቢሊዮን ዶላር ለመልሶ ግንባታው እንደሚያበረክቱ አስታውቀዋል።
በአጠቃላይ ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ሃገራቱ ከ650 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ለጋዛ ሰርጥ መልሶ ግንባታ ለመለገስ ቃል መግባታቸው ተጠቅሷል
ከ 50 ቀናት በኋላ በግብፅ አስተባባሪነት በተፈፀመ ወሰን የለሽ የተኩስ አቁም ስምምነት ነሐሴ 20 ፣ 2006 ዓ ም የጋዛው ጦርነት ማብቃቱ ይታወሳል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ልደት አበበ