የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ሊወጣ ነዉ | ኢትዮጵያ | DW | 29.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ሊወጣ ነዉ

የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር አጄንስ በመጭዉ ሳምንት ሐምሌ 30፣ 2008 የ20/80 እና የ10/90 የተባሉትን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለ11ኛ ግዜ ዕጣ ለማዉጣት እንዳቀደና ፣ለተጠቃምዉ ከ39,000 በላይ ቤቶችን ለማስተላለፍ እንደተዘጋጀ የአጄንስ ዋና ስራ አስካያጅ ሽመልስ ታምራት ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:30

ቤቶች ዕጣ

ቤቶቹ የሚገኙት በዋናነት በቦሌ እና አቃቅ ክፍለ ከተሞች ሲሆን ኮዬ ፈጬ፣ በቅልንጦ ስሆኑ የካ እና ሃያት በተባሉ ልዩ ስም የሚታወቁ የተለያዩ ፕሮጄክቶች እንዳሉም አቶ ሽሜሊስ ይናገራሉ።


መኖሪያ ቡቶቹን ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ስለሚወሰዱት ቅድመ ሁኔታዎች፣ ቀሪዉን 80 ወይም 90 ከመቶዉ ተጠቃሚዎች ቀስ በቀስ እንዲከፍሉ የተደረገበት አሰራር ምን ያህል የገቢ ምንጫቸዉን ያማከለ ነዉ ለሚለዉ ጥያቄ፣ እንድሁም ይህን ዕዳ ወይም ብድር መክፈል ካልቻሉ ሌሎች ኮንዶምንየሞች ላይ እንደሚደረገዉ ለሌላ አካል መሸጥ ይቻል እንደሆነ ላቀረብነው አቶ ሺሜልስ ማብራርያ ሰቶዋል። ለበለጠ መረጃ አዉድዮን ያዳምጡ።

በዚህ ጉዳይ ላይ በዶቼ ቬሌ ድረ ገፅ ላይ ያወያየናቸው አስተያየት ሰጭዎች የከተማዋ አመራሮች የተለያየ መግለጫ ውዥንብር ውስጥ እንዳስገባቸው፣ እነዚህ የጋራ ቤቶች ዝቅተኛ ገቢ ላለው ማህበረሰብ የታቀደ ነዉ ቢባልም ፣ አላማውን የሳተ ነው በሚል እቅዱን ተችተዋል።

መርጋ ዮናስ

አረያም ተክሌ

Audios and videos on the topic