የጋምቢያ ስደተኞች በጀርመን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 09.12.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጋምቢያ ስደተኞች በጀርመን

ጋምቢያን  ከ 21 ዓመታት በላይ የመሩት ፕሬዚዳንትነት ያህያ ጃሜ በተቃዋሚዉ መሪ መሸነፋቸዉን ተከትሎ በሃገሪቱ የሚታየዉ ደስታ እንደቀጠለ ነዉ። በሌላ በኩል በምዕራብ አዉሮጳ የሚኖሩ የጋምብያ ተገን ጠያቂዎች ፕሬዚዳንት የያህያ ጃሜ ከስልጣን መዉረድ ቢያስደስታቸዉም፣ 

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:55
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
02:55 ደቂቃ

በጀርመን የሚኖሩ የጋምቢያ ስደተኞች

በአዲስ ተመራጩ የጋምቢያ ፕሬዚዳንት አዳማ ባሮ ዘመነ ስልጣን ወደ ሃገራቸዉ ተመለሱ እንዳይባሉ ስጋት አድሮባቸዋል። 

የ 42 ዓመቱ ቡባካር ድራማ ባለፈዉ አርብ የተካሄደዉን የጋምብያን ምርጫ ሳስብ ገነት እንደገባ ሁሉ ይሰማኛል ሲል ፊቱ በደስታና ፈገግታ ይሞላል። በ «ዋትስ አፕ» ቡድን የመልክት መገናኛ በስመር በኩል የደረሰዉ በመጀመርያ መልክት በርግጥም «ቀልድ» ብሎ ነበር የወሰደዉ። በርግጥ የጋምቢያ ተቃዋሚዉ መሪ የአዳማ ባሮ ድል መቀዳጀትን ሲያረጋግጥ ደስታ ማብሰር መቀጠሉን ይናገራል። « ሁሉ ነገር ጥሩ ይሆናል የፀጥታ አስከባሪዎች ሁሉ ሳይቀሩ ነዉ ደስታቸዉን እየገለፁ የሚገኙት አለ» በበርሊን ነዋሪ የሆነዉ ጋምብያዊዉ ስደተኛ የዶቼ ቬለን ጋዜጠኛ በቀጠሮዉ መሰረት ሲያገኝ። እንድያም ሆኖ  ያ ሁሉ ደስታና ፈገግታ በአንድ ጊዜ ክስም አለ። ከጋዜጠኛዉ ጋር በነበረበት ክፍል ዓይኑን ከግራ ወደቀኝ እያማተረ ድምፁን ዝቅ አድርጎ መነጋገር ጀመረ። 

«በጀርመን የተገን ጥያቄ ሳቀርብ ሁሉ ነገር ጥሩ ነዉ ብዬ አስቤ ነበር። ለኛ ግን በዚህ ወቅት  ነገሩ   ከባድ ነዉ የሆነዉ ፤ ምክንያቱም በጋምብያ ሰላም በመስፈኑ ነዉ። እናም የተገን ጥያቄዬ ተቀባይነት የሚያገኝ አይመስለኝም።»

የጋምብያዊዉ ስደተኛ የተገን ጥያቄዉ ገና በእንጥልጥል ላይ በመሆኑ ትክክለኛ ስሙን መግለፅ አይፈልግም።  የጀርመን የሃገር አስተዳደር ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንደሚሉት በጀርመን በርካታ የጋምቢያ ስደተኞች ይገኛሉ። ከነዚህ ስደተኞችም ጋር ብዙ ችግሮች አሉብን ሲሉ ከጋምቢያ ምርጫ በፊት የቫድንቡተንበርግ ግዛት የአስተዳደር  ቶማስ ሽትረብል ተናግረዋል። እንደ ዚሁ መሥርያ ቤት መረጃ በጀርመን ከሚኖሩት 14,500 የጋምቢያ ዜጎች መካከል ስምንት ከመቶ የሚሆኑት የጋምቢያ ተወላጆች በእጽ ዝዉዉርና ንግድ  አሉበት ይባላል። በጀርመን ከአፍሪቃ ሃገራት ከመጡ ስደተኞች መካከል የጋምቢያ ዜጎች በቁጥር ብዛት ሦስተና ደረጃ ላይ ይገኛሉ።  በጀርመን የሚገኙ ተገን ማመልከቻቸው ገና መልስ ያላገኘላቸው ስደተኞች በሕጋዊ መንገድ ሥራ እንዲሰሩ አይፈቀድላቸዉም። አብዛኞቹ ስደተኞች ደግሞ ወደ አዉሮጳ ለመግባት በተለያዩ ጉዳዮች ድጋፍ ያደረጉላቸዉን  ቤተሠቦቻቸዉን መርዳት ይሻሉ፤ በዚህም ምክንያት አብዛኞች ወደ ንግዱ ዓለም እንዲገቡ መገደዳቸዉ ተመልክቶአል።    

ጀርመናዊዉ ወግ አጥባቂ ፖለቲከኛ ሽትረብል በጀርመን የተገን ጥያቄአቸው ውድቅ የሆነባቸውን ስደተኞች መንግሥት ወደ የሃገራቸዉ እንዲመልስ በየጊዜዉ ሲወተዉቱ ይሰማል።  ዴሞክራሲ የፈነጠቀባት ጋምቢያ አስተማማኝ በሚባሉ ሃገራት ተርታ ስር መመደብ ስለምትችል ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞችን ወደዚችው ሀገር ለመመለስ ከባድ አይደለም የሚል አቋምም አላቸዉ።

የጀርመን ሃገር አስተዳደር ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቶብያስ ፕላተ እንደገለፁት ጋምቢያ አስተማማኝ ሃገር ተብላ ስለመቀመጥ አለመቀመጥዋ የሚያዉቁት ነገር የለም።  በሌላ በኩል የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ አባል የሆኑትና የጀርመን ፓርላማ አፍሪቃ ጉዳይዩች ተጠሪዉ ክሪስቶፍ ሽትረሰር ስደተኞችን ስለመመለሱ ጉዳይ መነጋገሩ ትክክል አለመሆኑን ይናገራሉ።

«ይህን አይነት ዉይይት አጥብቄ እቃወማለሁ። ከሁሉ በላይ በአሁኑ ወቅት ይህች ሃገር ወዴት ልታመራ እንደምትችል አናዉቅም።  ባለፈው ሚያዝያ ዉስጥ እንኳን የታሰሩ የመንግስት ተቃዋሚዎች ስለመኖራቸዉ ማረጋገጫ አለን። በእስር ቤቶች ስቃይና እንግልት እንደሚደርስም ማስረጃ ይዘናል። ሁላችንም በምርጫዉ ዉጤት ደስተኞች ብንሆንም፣  ይህ አሁን የተጀመረው ውይይት በጋምብያ ያለውን እዉነታ ያላገናዘበ ነው። »  

 ቡባካር ድራማ ነኝ ሲል ስሙን የሚናገረዉ በበርሊን ነዋሪዉ የጋምቢያ ስደተኛም ለጀርመን መንግሥት ያቀረበዉ የተገን ጥያቄ መልስ እስኪያገኝ በፀጥታና ጥሞና መጠበቅን ይሻል። 

 

አዜብ ታደሰ / ዳንኤል ፔልዝ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic