የጊኒ ቢሳው ፕሬዚደንት ሞት | አፍሪቃ | DW | 04.02.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የጊኒ ቢሳው ፕሬዚደንት ሞት

የንዑስዋ ምዕራብ አፍሪቃዊት ሀገር ጊኒ ቢሳው ፕሬዚደንት ማላም ባካይ ሳንሃ ባለፈው ሰኞ በአንድ የፓሪስ ሐኪም ቤት አረፉ።

default

ፕሬዚደንት ማላም ባካይ ሳንሃ

 በ 2009 ዓም በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት የስድሳ አራት ዓመቱ ፕሬዚደንት ሳንሃ በተለይ በፖለቲካው ዘርፍ የጦር ኃይሉ ተፅዕኖ ከፍተኛ በሆነባት በጊኒ ቢሳው መረጋጋት የማምጣቱን ተግባር ዋነኛው ዓላማቸው አድርገው ነበር። የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ሄለን ደ ጉቬያ እንደዘገበችው፡የሱስ አስያዥ ዕፅ ንግድ ያስፋፉት እና ለኮኬይን ንግድ ማጓጓዣው ተግባር ጊኒ ቢሳውን እንደ መተላለፊያ የተጠቀሙባትና አሁንም የሚጠቀሙባት የደቡብ አሜሪካ ሕገ ወጥ ቡድኖችም በዚችው ምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ውስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳርፈዋል። የዛሬው ዝግጅት ባለፉት ዓመታት በርካታ መፈንቅለ መንግሥት እና ግድያ የተካሄደባትን ጊኒ ቢሳው ለማረጋጋት ስለሞከሩት ማቹ ርዕሰ ብሔር ማላም ባካይ ሳንሃ ማን እንደነበሩ  ባጭሩ ይመለከታል።

አርያም ተክሌ

መሥፍን መኮንን

Audios and videos on the topic

 • ቀን 04.02.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/13jXu
 • ቀን 04.02.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/13jXu