የገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ(ገሞራዉ ዜና እረፍት) | ባህል | DW | 12.11.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

የገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ(ገሞራዉ ዜና እረፍት)

ባለፈዉ ዕሁድ በስደት በሚኖርበት ስዊድን ሐገር ያረፈዉ የኢትዮጵያዊው ባለቅኔ የኃይሉ ገብረዮሐንስ‬ (ገሞራው) የቀብር ሥነ-ሥርዓት ሰሞኑን እንደሚፈጸም ወዳጆቹ አስታወቁ።ኃይሉ በኢትዮጵያ ዘመናይ ሥነ-ፅሁፍ ሥመ ጥር ከነበሩ ደራሲዎች አንዱ ነበር።

ይሁንና በስራዎቹ ምክንያት በተደጋጋሚ እስር፤ እንግልት እና በመጨረሻም ተዳርጎ ሕይወቱም በስደት አልፋለች።

ኃይሉገብረዮሐንስወይም(ገሞራው) የተወለደው እ.ኤ.አ. በ1935 አዲስ አበባ ውስጥ ነበር። በአባቱ በመርጌታ ገብረዮሃንስ በጀመረዉ የቤተ ክሕነት ትምህርት እስከ ስነ-መለኮት ኮሌጅ ዘልቋል። ጎን ለጎን የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ምኒሊክ ትምሕር ቤት አጠናቀቀ።እና ቀድሞ አፄ ሐይለ ስላሴ ይባል በነበረዉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎች ጥናት ተቋም የመጀመሪያ ዲግሪዉን አግኝቷል። የኢትዮጵያ ተማሪዎች ዘዉዳዊዉን አገዛዝ በመቃወም እንቅስቃሴ በተጀመሩበት ዘመን ኃይሉ በግዕዝ፤አማርኛና እንግሊዘኛ በሚጽፋቸው ተቺ ግጥሞች በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዘንድ ከፍ ያለ ተቀባይነት አግኝቶ ነበር። ሐይሉና ሥራዎቹን በቅርብ የሚያዉቀዉ ደራሲ ደራሲ ሐማ ቱማ እንደሚለዉ የሐይሉ የሰላ ትችት ግን በወቅቱ የነበረው ንጉሳዊ መንግስት ዘንድ በአይነቁራኛ እንዲታይ ምክንያት ሆኗል።

ኃይሉ ገብረዮሐንስ(ገሞራው) ሲታወስ በቀዳሚነት ከሚነሱት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካነበቧቸው ግጥሞች መካከል 'በረከተ-መርገም' አንዱ ነው። ኃይሉ ገብረዮሐንስከዚህ ግጥም ባሻገር በርካታ ስራዎችን ማበርከቱን አለሙ ተበጀ ይናገራሉ። ሞገደኛው ገጣሚ ኃይሉ ገብረዮሐንስበመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች በመምህርነት ሙያ አገልግሏል። ቤጂንግ ዩኒቨርሲቲ-ቻይና ለከፍተኛ ትምህርት ከኢትዮጵያ የወጣዉ ኃይሉ የንጉሱ ሥርዓት ከተወገደ በኋላም በፖለቲካ አቋሙ ምክንያት ወደ ሃገር መመለስ አልቻለም።እንደገና ደራሲ ሃማ ቱማ ይናገራሉ።

ገጣሚ ኃይሉ ገብረዮሐንስወይም ገሞራው በስደት በኖረባቸው አመታት የህጻናትና የታሪክ ማስተማሪያ መጻህፍትን ጨምሮ በርካታ ስራዎችን ለማሳተም እየጣረ ነበረ።መጀመሪ ሕመም፤ አሁን ደግሞ ሞት ቀደመዉ። ኃይሉ ገብረዮሐንስ(ገሞራው) የቀብር ስነ-ስርዓት በስደት በኖረበት ስዊድን ሃገር እንደሚፈፀም ወዳጆቻቸው እና አድናቂዎቻቸዉ ገልጸዋል።

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic