የገንዘብ እርዳታ ለሰማዕታት ቤተሰቦች | ኢትዮጵያ | DW | 03.07.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የገንዘብ እርዳታ ለሰማዕታት ቤተሰቦች

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቤተክህነት በተካሄደ ስነስርዓት ላይ እንደተገለፀው ስዊዝ ነዋሪ የሆኑት ኢትዮጵያውያን ሊቢያ ውስጥ በግፍ ለተገደሉት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ሰማዕታት ቤተሰቦችና ወላጆች ከ400 ሺህ ብር በላይ ነው ያዋጡት።


በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከሁለት ወር በፊት ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ በሚጠራው ፅንፈኛ ቡድን ሊቢያ ውስጥ በአረመኔያዊ ግድያ ህይወታቸው ላለፈ ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት ወላጆች እና ቤተሰቦች ያሰባሰቡትን ገንዘብ አበረከቱ። ትናንት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቤተክህነት በተካሄደ ስነስርዓት ላይ እንደተገለፀው ስዊዝ ነዋሪ የሆኑት ኢትዮጵያውያን ሊቢያ ውስጥ በግፍ ለተገደሉት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ሰማዕታት ቤተሰቦችና ወላጆች ከ400 ሺህ ብር በላይ ነው ያዋጡት። በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic