የገና ገበያና የጀርመን ኤኮኖሚ | ኤኮኖሚ | DW | 25.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የገና ገበያና የጀርመን ኤኮኖሚ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ይላሉ ፤ በበዓሉ ለልብስ ገንዘብ ለማውጣት መሳሳት እንደማይገባ ለማስገንዘብ ።

እዚህ ጀርመን ደግሞ ለገና ያልወጣ ገንዘብ…… የሚል አባባል ባይኖርም ለበዓሉ ብዙ ገንዘብ ማውጣት የተለመደ ነው ። ለስጦታ ፣ ለድግስ ፣ ለአልባሳት ለቤት እቃ ና ለመዝናኛ ብዙ ገንዘብ ከሚፈስባቸው በዓላት ገና ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል ። ባለፈው ህዳርና በመገባደድ ላይ ባለው በታህሳስ ወር ብቻ ጀርመኖች ለገና ገበያ ያወጡት ገንዘብ ከ80 ቢሊዮን ዩሮ ይበልጣል ። ይህም የጀርመንን ኤኮኖሚ በማንቀሳቀስና በመታደግ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዘግቧል ። ይልማ ከሰሞኑ በየገበያው ተዘዋውሮ የተመለከተውን እንዲሁም የዶቼቬለዎቹ Viktoria Klebe ና Madeleine Meier የዘገቡትን በዛሬው የኤኮኖሚው ዓለም ዝግጅት ያቀርብልናል ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic