የገና በዓል አከባበር | ኢትዮጵያ | DW | 07.01.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የገና በዓል አከባበር

የገና በዓል ልዩ ዝግጅት በተመለከተ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ የአውሮጳ ሃገራት የሚገኙ ወኪሎቻችን የላኩት ዘገባ በተለይ በአውሮጳ የሚገኙ ስደተኞች በዓሉን እንዴት እንዳከበሩት ያስቃኛል። ዘገባዎቹ ከኢትዮጵያ፣ ከፈረንሣይ፣ ከጀርመን እና ከጣሊያን የተላኩ ናቸው።

የአዲስ አበባው ወኪላችን ዩሀንስ ገብረእግዚያብሄር በመዲና አዲስ አበባ ዞር ዞር እያለና ወደ ሌላ ከተማም ስልክ በመደወል በዓሉ እንዴት እየተከበረ እንደሆነ አጠያይቋል።

የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል በመዲና በርሊን እና አከባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን አነጋግሮአል።

ፓሪስ ከተማ የሚገኙ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የበዓል መንፈሱ ቀስ በቀስ እየጠፋባቸው እንደሆነ ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ ባገኙት አጋጣቢ በዓሉን አክብረው እንደሚውሉ ለፓሪሷ ወኪላችን ሐይማኖት ጥሩነህ ገልፀውላታል። በተለይ በስደት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዓሉን እንዴት አከበሩት ሐይማኖት ጥሩነህ ገልፃልናለች።

ሮም የሚገኘው የዶይቸ ቬለ ወኪል ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስም እንዲሁ ፤ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ስደተኞች በዓሉን እንዴት እንደሚያከብሩ ከሮም ዘገባ ልኮልናል።

ሁሉንም ከዚህ በታች በድምፅ ያገኛሉ።

ልደት አበበ / ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic