የገቢዎች ሚኒስቴር እርዳታ ለተፈናቃዮች  | ኢትዮጵያ | DW | 21.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የገቢዎች ሚኒስቴር እርዳታ ለተፈናቃዮች 

ሚኒስቴሩ ድጋፉ በሁሉም ክልሎች የሚቀጥል እንደሆነና ከዚህ በፊትም 100 ሚሊዮን ብር ያህል ዋጋ ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ ለ ጌድዮ ተፈናቃዮች መለገሱን አስታውቋል፡፡ በተመሳሳይ  ሁኔታ በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተሰበሰበ ግምቱ 25 ሚሊዮን የሚሆን ሸቀጣሸቀጥ ለጌዲዮ ተፈናቃዮች ተጓጉዟል

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:27

የገቢዎች ሚኒስቴር እርዳታ

የገቢዎች ሚኒስቴር በኦሮሚያ ክልል ለተፈናቀሉ እና በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ዜጎች ግምቱ 52 ሚሊዮን ብር የሚሆን በኮንትሮባንድ የተያዘ አልባሳት ፡ የምግብ ዘይት እና ስኳር ድጋፍ አደረገ፡፡ ሚኒስቴሩ ድጋፉ በሁሉም ክልሎች የሚቀጥል እንደሆነና ከዚህ በፊትም 100 ሚሊዮን ብር ያህል ዋጋ ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ ለ ጌድዮ ተፈናቃዮች መለገሱን አስታውቋል፡፡ በተመሳሳይ  ሁኔታ በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተሰበሰበ ግምቱ 25 ሚሊዮን የሚሆን ሸቀጣሸቀጥ ለጌዲዮ ተፈናቃዮች ተጓጉዟል።ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ 

Audios and videos on the topic