የገልፍ ባሕረሰላጤ ሃገራት ውዝግብ እና አፍሪቃ | አፍሪቃ | DW | 17.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የገልፍ ባሕረሰላጤ ሃገራት ውዝግብ እና አፍሪቃ

በገልፍ ባሕረሰላጤ ሃገራት ማለትም በሳዑዲ ዓረቢያ እና ተባባሪዎቿ እንዲሁም በካታር መካከል የተፈጠረው እሰጥ አገባ መዘዙ ወደሌሎች ሃገራት እንዳይሻገርም አስግቷል። ካታር ጦሯን ከጅቡቲ ማስወጣቷን ተከትሎ በጅቡቲ እና በኤርትራ መካከል የድንበር ውጥረት ነግሷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 18:21

ትኩረት በአፍሪቃ

በገልፍ ባሕረ ሰላጤ ሃገራት መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ተጽዕኖውን በአፍሪቃ ሃገራት ላይም ማሳረፍ ጀምሯል። በይዞታ ይገባኛል ሲወዛገቡ የቆዩት ጅቡቲ እና ኤርትራ በድንበራቸው ሰፍሮ የነበረው የኳታር ጦር ሰራዊት በዚህ ሳምንት አካባቢውን ለቅቆ ከወጣ በኋላ ወደ ውጥረት ውስጥ ገብተዋል፡፡ የኤርትራ ወታደሮች በድንበር ላይ የሚገኘውን ዱሜራ ተራራ ተቆጣጥረዋል ስትል ጅቡቲ ትከስሳለች፡፡ ይህንንም ለአፍሪቃ ኅህብረት በይፋ ማሳወቋን የኅብረቱ ቃል አቃባይ ኤባ ካላንዶ ለአሶሴትድ ፕሬስ ዜና ምንጭ ተናግረዋል፡፡

የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት ኅብረቱ በሁለቱ ሀገራት ድንበር ያለውን ሁኔታ ለመከታታል አንድ ቡድን ወደ ቦታው እንደሚልክ አሳውቀዋል፡፡ ኅብረቱ “ከሁሉም ወገኖች ጋር እንደሚሠራም” ገልጸዋል፡፡ ኤርትራ በጅቡቲ በኩል ስለሚቀርብባት ውንጅላ ይፋዊ ምላሽ እስካሁን አልሰጠችም፡፡ ኤርትራ «450 ግድም የሚደርሰው የካታር ሰላም አስከባሪ ጦር ከጅቡቲ ለምን እንደወጣ እስካሁን ማብራሪያ አልሰጠም» ብላለች። የትኩረት በአፍሪቃ ቀዳሚው ርእስ ነው። የአውሮጳ ኅብረት በናይጀሪያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የመልሶ ማቋቋም የሚውል 143 ሚሊዮን ዩሮ የልማት ርዳታ ለግሷል። ሌላው በትኩረት በአፍሪቃ የተዳሰሰ ርእስ ነው። 

ገበያው ንጉሤ/ ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ተስፋለም ወልደየስ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic