የጅቡቲ ወደብን የማቃለል ሥራ | አፍሪቃ | DW | 07.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የጅቡቲ ወደብን የማቃለል ሥራ

በከፋ ድርቅ የተጠቃችዉ ኢትዮጵያ የምግብ እጥረት ለገጠመዉ ቢያንስ 10 ሚሊዮን ሕዝቧ ምግብ ከዉጭ ማስገባት አለባይኖርባታል። የምግብ ርዳታን ለማድረስ በጅቡቲ ወደብ በኩል የተላከዉ የዉጭ ርዳታና ሃገሪቱ ያስመጣችዉ ምግብ በወደቡ ላይ በተከሰተዉ የመርከብ መጨናነቅ መዉረድ አለመቻሉ ተሰምቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:09

የተጨናነቀዉ ወደብ ለማቃለል

ይህን ችግር ለመቅረፍ በጅቡቲ ወደብ ተጨማሪ የወደብ ሰራተኞች ከመርከቡ ላይ ጭነትን በማዉረድና በመጓጓዝ ሥራን ጀምረዋል። ከዚህ ሌላ ወደቡ ላይ የቆመዉን እቃ ለሟጓጓዝ እንዲያስችል አዲስ የባቡር መስመር ዝርጋታ ተጠናቆ ሥራዉን ጀምሮአል። ሰኔ አጋማሽ ዉስጥ ነዉ በተጨናነቀዉ የጅቡቲ ወደብ በየቦታዉ ተቆልሎ የጆንያ ስንዴ ቆሟል የጭነት መኪናዎች ይህን የተከማቸ ጆንያ ስንዴ ጭነዉ ለሟጓጓዝ ተሰልፈዉ ተራቸዉን ይጠባበቃሉ። የጭነት ማመላለሻዎቹ ተሽከርካሪዎች ወደቡ አጠገብ በጆንያ የተደረደረዉን እህል ከጫኑ በኋላ ከአስርት ዓመታት በኋላ ከፍተኛ ድርቅ ለተመታዉ ለኢትዮጵያ ነዋሪ ለማድረስ ጉዞዎአቸዉን በስተምዕራብ ወደ ኢትዮጵያ አቅጣጫ ጉዞአቸዉን ይጀምራሉ። ወደቡ ላይ በርካታ ሰራተኞች ከመርከብ ላይ ጭነትን ቶሎ ለማዉረድ ሥራ ላይ ቢሰማሩም የምግብ እህልን ይዘዉ ጅቡቲ ወደብ ከደረሱት መርከቦች ጭነትን ቶሎ አራግፈዉ መጨረስ አልቻሉም። እንደ ጅቡቲ ወደብ ድረ-ገጽ መረጃ ሰኔ መጨረሻ ላይ አሁንም 16 መርከቦች 609 ሺ ሜትሪክ ቶን ስንዴ፤ ገብስና ማሽላን እንዲሁም ማዳበርያን ጭነዉ የሚያራግፋቸዉ እስኪያገኙ ቆመዋል። የጅቡቲ ወደብ ሥራ አስኪያጅና የነፃ ዞን ባለስልጣን አቡበከር ኦመር በወደቡ ላይ ስለሚታየዉ ችግር እንዲህ ያስረዳሉ፤
« ሁኔታዉ በትውሰነ ደረጃ ተሻሽሎአል።

ቢሆንም ግን አሁንም በርካታ የርዳታ እህልና ማዳበርያ ጭነዉ የቆሙ መርከቦች ይገኛሉ። ማዳበርያዉ የዘር ወራት በማብቃቱ አሁን ተፈላጊነቱ እየወረደ ነዉ። የምግብ ርዳታና ማዳበርያን የጫኑት የጭነት ማመላለሻ መርከቦቹ ወደቡ ላይ የደረሱት በአንድ ወቅት ነዉ። አንዱን ከአንዱ አስበልጦ መቀበሉ ለኛ በጣም ፈታኝ ሁኔታ ነበር፤ ግልፅ ነዉ ቅድምያ የሰጠነዉ ለምግቡ ነበር። ከዝያ ደግሞ ለገበሪዎቹ ማዳበርያዉን በወቅቱ ማድረስ የሚለዉ ፈተና ገጠመን። ግን ዋናዉ ችግሩ ያለዉ ወደቡ ላይ ሳይሆን በሃገር ዉስጥ ያለዉ የመጓጓዣ ጉዳይ ነዉ። የርዳታዉን እህልና ማዳበርያዉን የሚያጓጉዙ በቂ የጭነት ማመላለሻዎች የሉም። »ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪቃ ሃገራት መካከል በከፍተኛ መጠን ስንዴ የምትጠቅመዉ ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የምግብ እጥረት ለመቋቋም የስንዴ ምርት ግዥን ከፍ ለማድረግ ተገዳለች። ድርቅ ባስከተለዉ ጉዳት በሃገሪቱ ከ 50 እስከ 90 በመቶ የሚሆነዉ አዝመራ ምርትን አልያዘም።

በሟጓጓዣ እጥረት ጅቡቲ ወደብ ላይ በተፈጠረዉ መጨናነቅ፤ ለኢትዮጵያ ያላትን ፍላጎት የሚወሳት ሳይሆን ጅቡቲ ወደብ ላይ ምን ያህል ጥገኛ መሆንዋን ነዉ። ኢትዮጵያ ለዉጭ የምታቀርበዉ የንግድ ቁሳቁስ 90 % የሚያልፈዉም በጅቡቲ ወደብ በኩል ነዉ። በጎርጎረሳዉያኑ 2005 ዓ,ም ሃገሪቱበዚህ ወደብ በኩል ወደ ዉጭ የምትልከዉ ሁለት ሚሊዮን ቶን ነበር፤ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ 11 ቶን ሆንዋል። በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ወደ 15 ቶን እንደመጨምርም ተመልክቶአል። ይህ የዉጭ ፍላጎት ኢትዮጵያን በአካባቢዉ ልዩ ቦታ ያሰጣታል ያሉት የወደብ ጉዳይ ባለሥልጣን አቶ ዳዊት ገብረአብ፤
«ኢትዮጵያ ለአካባቢዉ ሃገራት እንደ ባቡር ማለት ናት። ይህ የሆነዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚኖረዉን ወደ 100 ሚሊዮን ሕዝብ ማየት ይቻላል። ብዙ ተጠቃሚ ያለበት ቦታ ነዉ ። አቅርቦትና አገልግሎት ያስፈልጋቸዋል። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ አካባቢ ለሚገኙ ሃገራት ከፍተኛ ገበያ ዉስጥ ለመግባት ትልቅ አጋጣሚ ነዉ። በርግጥም ይህ አጋጣሚ በሁለቱም በኩል የሚታይ ይሆናል።»


ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከሶማሌላንድ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር የተለያዩ የመግባብያ ስምምነቶችን ፈጽማለች።
756 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለዉ የጅቡቲ ኢትዮጵያ የባቡር መስመር በጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ,ም ቢጠናቀቅም፤ ሥራዉን ግን ሙሉ በሙሉ አልጀመረም። በዚህ የባቡር መስመር በቀን 2000 ቶን የምግብ እህልን በማመላለስ በጅቡቲ ወደብ የሚታየዉን ችግር ማቃለል እንደሚቻል የወደቡ ሥራ አስፈጻሚ አቡበከር ኦመር ተናግረዋል። የባቡር መስመሩ ሙሉ በሙሉ ሥራዉን ሲጀምር እንዲሁም በሚቀጥለዉ መስከረም ወር የኤሌትሪክ ኃይል ሲያገኝ እያንዳንዳቸዉ 3500 ቶን መጫን አምስት ባቡሮችር መጓጓዝ ይቻላል።


ከዚህ በተጨማሪ ጅቡቲ መርከቦች ሊራገፉ የሚችሉበት ሌሎች ሦስት ወደቦችን ለመክፈት እቅድ ይዛለች። እንደ የጅቡቲ ወደብ ዋና ሥራ አስኪያጅና የነፃ ዞን ባለስልጣን አቡበከር ኦመር ገለፃ ፤ አዲሱ የጅቡቲ ወደብ « ታድጆራ » እስከ ባህርዳር የሚደርስ የባቡር መስመር መገናኛ ይኖረዋል። ይህ የባቡር መስመር ዝርጋታ አሁን በግንባታ ላይ ካለዉ ከአዋሽ መቀሌ የባቡር መስመር ጋር የሚገናኝም ይሆናል።


« ጅቡቲና ኢትዮጵያ በጋራ በጣም ከፍተኛ ሥራን እየሰሩ ነዉ። የሁለቱን ሃገራት የረጅም ጊዜ የሥራ እቅድ ያየን እንደሆነ በመሠረተ ልማት በንግድ ግንኙነት በፖለቲካዉ ዘርፍ በልማቱ ረገድ የጋራ አጀንዳ ለማበጀት እየሰሩ ናቸዉ። እንዲህ አይነቱ ግንኙነት የአፍሪቃ ልማት ባንክ በመሳሰሉት አጋሮች ተወድሶአል። ሁለታችንም አንዱ አንዱ ላይ ጥገኛ ሳንሆን በእኩል ደረጃ የምንጠቃቀም ነን»


ጀምስ ጀፍሪ / አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሠ

Audios and videos on the topic