የጅቡቲ ኤርትራ የድንበር ዉዝግብና የአፍሪቃ ኅብረት ዉሳኔ  | ኢትዮጵያ | DW | 04.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጅቡቲ ኤርትራ የድንበር ዉዝግብና የአፍሪቃ ኅብረት ዉሳኔ 

በጅቡቲ እና በኤርትራ መካከል ዉዝግቡ በተካረረበት በዚህ ወቅት የአፍሪቃ ኅብረት ወደ አስመራ ልዑካኑን እንደሚልክ ዛሬ አስታወቀ። ኅብረቱ ለቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ እና ለቀድሞዉ የጋና ፕሬዚዳንት ክዋሜ ኑክሩማ ሐዉልት ለማቆም በሙሉ ድምፅ ወስኖአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:16

ለቀዳማዊ ኃይለ ስላሴና ለኑክሩማ ሐዉልት ለማቆም ወስኖአል።ማክሰኞ ከቀትር በኋላ የተጠናቀቀዉ 29ኛዉ የአፍሪቃ ኋብረት የመሪዎች ጉባኤ የኅብረቱ ሊቀመንበር ሙሳ ፈቂ መሃማት እንዳመለከቱት የኤርትራ ወታደሮች አወዛጋቢዉን የራስ ዱሜራ ተራራ አካባቢ ወርረዋል ስትል ጅቡቲ ክስ ወዳቀረበችባት ኤርትራ መልዕክተኞችን እንደሚልኩ መናገራቸዉን ቦታዉ ላይ የተገኘዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኋይለጊዮርጊስ በስልክ ነግሮናል። ኅብረቱ በተጨማሪ ከተነጋገረባቸዉ ዋና ዋና ነጥቦች መካከል በተለይ በአህጉሪቱ ለሚገኘዉ ወጣት ሥራ አጦች የሥራ እድልን መፍጠር እና፤ ኅብረቱ የሚንቀሳቀስበት የፊናንስ ጉዳይ ነበሩ። በሌላ በኩል ለቀዳማዊ ኃይለስላሴ እና ለቀድሞዉ የጋና ፕሬዚዳንት ክዋሜ ኑክሩማ ኃዉልት ለማቆም ኅብረቱ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን ቦታዉ ላይ የነበረዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን በስልክ ነግሮናል። 

ጌታቸዉ ተድላ ኋይለጊዮርጊስ 


አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic