የጄኒን ልብ | ባህል | DW | 11.05.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የጄኒን ልብ

የሰው ልጅ በሙዚቃ አለያም በስዕል ጥበብ ሊበቀል ይችላል። በዚያ ወታደር አይገድልም። የሠብአዊነት ተግባሬ እስራኤሎችን ይረብሻቸዋል። ለብዙዎቹ አየር ላይ ብጎን ደስታቸው ነበር። እነሱ አንድ ፍልስጥኤማዊ አንድ እስራኤላዊ ህፃንን ከሚታደግ ይልቅ ሲገድል ቢያዩ ይወዱ ነበር።

default

ግጭት የማያጣው አካባቢ

የአስራ ሁለት ዓመቱ ፍልስጤማዊ ህፃን ከሌሎች ህፃናት ጋር እውነተኛ ባልሆነ መሳሪያ እየተጫወተ ነው። በቅፅበት ግን በእውነተኛው የጦር መሳሪያ በእስራኤል ወታደሮች ይተኮስበትና ህይወቱ ታልፋላች። ወላጅ አባቱም የህፃኑ አንዳንድ የሰውነት ክፍል ለህመምተኛ እስራኤላውያን ህፃናት በህክምና ዘዴ እንዲዛወርና ህፃናቱ ከሞት እንዲተርፉ ይፈቅዳሉ። በዚህ እውነተኛ ታሪክ ዙሪያ የሚያጠነጥን ዘጋቢ ፊልም ተሰርቶ ለእይታ ቀርቧል። የጄኒን ልብ የተሰኘውይህ ፊልም ብዙዎችን አድደምሟል። የዶቸቬለዋ ሳራ ሜርሽ ፊልሙን ተመልክታዋላች በሚከተለው መልኩ ተቀናብሯል።

ZPR

ማንተጋፍቶት ስለሺ