የጂዮርጂያ ምክር ቤታዊ ምርጫ ውጤት | ዓለም | DW | 02.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የጂዮርጂያ ምክር ቤታዊ ምርጫ ውጤት

በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ሬፓብሊክ ጂዮርጂያ ትናንት በተካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ ቢድዚን ኢቫንሽቪሊ የሚመሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት ቀናው።

ጆርጂያ ዉስጥ በተካሄደዉ ምክር ቤታዊ ምርጫ «የጆርጅያ ህልም» የተሰኘዉ ተቃዋሚ ፓርቲ ድል ቀናዉ። በቀድሞዋ የሶቪየት ኅብረት ሪፑብሊክ ስልጣን የሙጥኝ እንዳለ ይቀጥላል ተብሎ የተሰጋዉ ገዢ ፓርቲ በተቃዋሚነት እንደሚቀጥል ፕሬዝደንት ሚኻኢል ሻኻስቪሊ ይፋ ማድረጋቸዉን የጀርመን የዜና ወኪል ከቲቢሊሲ ዘግቧል። ዴሞክራሲ አሸነፈ ያሉት ሻካስቪሊ ተቃዋሚዉ የጆርጂያ ህልም የተሰኘዉ ፓርቲ ምርጫዉን ማሸነፉን ተናግረዋል። በሺዎች የተገመቱ ደጋፊዎች የመዲና ቲቢሊሲ ጎዳናዎችን በአዉቶሞቢል ጡሩምባ ድምፅ፤ እንዲሁም ሰማያዊዉን የፓርቲዉን አርማ እና ቀይ በነጭ የሆነዉን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ በማዉለብለብ ደስታቸዉን ሲገልፁ ዉለዋል።

Georgien Parlamentswahl Bidzina Ivanishvili Tbilisi

ቢድሲና ሊቫንሽቪሊ


ዘገባዎች እንደሚሉት በቢሊዮነሩ ነጋዴ ቢድሲና ሊቫንሽቪሊ የሚመራዉ የጆርጅያ ህልም የመራጩን 53 በመቶ ድምፅ ሲያገኝ የሳካሽቪሊ ገዢ ፓርቲ ደግሞ በ41 በመቶ ተወስኗል። ሊቫንሽቪሊ በጆርጂያ ታሪክ የህዝቡ ድምፅ የስልጣን ሽግግርን እንዳረጋገጠ ነዉ የተናገሩት፤
«በጆርጂያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ህዝብ በምርጫ የስልጣን ለዉጥን መምራት ቻለ። አሁን በጋራ ባለፈዉ የተደረገዉን በመርሳት አዲሲቷን ጆርጂያ መገንባት ይኖርብናል። ቢያንስ አንድ መቶ የምክር ቤት መቀመጫ የእኛ ነዉ።»ያለፉት ዘጠኝ ዓመታት ሀገሪቱን የመሩት የፕሬዚደንት ሚካኤል ዛካሽቪሊ ጠንካራ ተፎካካሪ የሆኑት ቢልየኔሩ ኢቫንሽቢሊ ከመራጭ ድምፅ መካከል 53%፣ ፕሬዚደንት ሚካኤል ዛካሽቪሊ ደግሞ 41% አግኝተዋል። ፕሬዚደንት ሚካኤል ዛካሽቪሊ በሀገራቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ የተደረገውን የሥልጣን ለውጥ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል።

ክሪስቲነ ናግል
ይልማ ኃይለሚካኤል
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic