የጀግኖቹ አትሌቶች አዲስ አበባ መግባት | ኢትዮጵያ | DW | 28.08.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጀግኖቹ አትሌቶች አዲስ አበባ መግባት

በሀያ ዘጠነኛው የቤይዢንግ ኦሊምፒያደ የተሳተፈው የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅና ስሜት የሚነካ አቀባበል ተደረገለት።

ጥሩነሽ ዲባባ

ጥሩነሽ ዲባባ

ቡድኑ ሰባት ሜዳልያዎችን በማግኘት በማግኘት ከዓለም አስራ ስምንተኛ ፡ ከአፍሪቃ ደግሞ ጎረቤት ኬንያን ተከትሎ የሁለተኛነቱን ቦታ ይዞዋል። በወንዶች የአስር ሲህና የአምስት ሺህ የሩጫ ውድድር ቀነኒሳ በቀለ፡ በሴቶች የአስር ሲህና የአምስት ሺህ የሩጫ ውድድር ጥሩነሽ ዲባባ እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት የወርቅ ሜዳልያ ሲያገኙ፡ ስህነ ስለሺ በወንዶች የአስር ሺህ የሩጫ ውድድር የብር ሜዳልያ፡ መሰረት ደፋር ደግሞ በሴቶች የአምስት ሺህ የሩጫ ውድድር የነሀስ ሜዳልያ፡፡በመጨረሻም ጸጋየ ከበደ በማራቶን ውድድር የነሀስ ሜዳልያ ባለቤቶች ሆነዋል። ወኪላችን ታደሰ እንግዳው በአትሌቶቹ አቀባበል ስነስርዓት የተገኙትን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቤተሰብ መሪና ደጋፊ አቶ አቤሴሎም ይሕደጎንና የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ መምሪያ ተወካይ ሿምበል ሙሉጌታ መለሰን አነጋግሮ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።