የጀርመን 21ኛ አመት ዉህደት ድግስ | ባህል | DW | 06.10.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የጀርመን 21ኛ አመት ዉህደት ድግስ

ጀርመን በሁለት ርዕዮተ አለም ከፍሎአት የቆየዉን ግንብ ገርስሳ አንድ በመሆን የተዋሃደችበትን ሃያ አንደኛ አመት በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ ሰኞ እለት በደማቅ አክብራ ዉላለች።

default

የቦን ከተማ ድግስ

ዘንድሮ ይህ ክብረ በአል በቀድሞዋ የምዕራብ ጀርመን ዋና መዲና ቦን ከተማ ላይ መደረጉ፣ ሁለቱ ጀርመኖች ከተዋሃዱ በኋላ ዋና መዲናዋ ወደ ሆነችዉ ወደ በርሊን የተጓዙትን የመንግስት ባለስልጣናት እና የሚኒስቴር መስርያ ቤት ባልደረቦች ወደ ቀድሞዊትዋ መዲና ቦን ከተማ በእንግድነት እንዲመጡ ጋብዞአል። በርካታ ጀርመናዉያን ታሪካቸዉን ለመረዳት ደስታቸዉንም ለመጋራት ቦን የዉህደት ቀን በአል ላይ ተገኝተዋል። ቦን ዘንድሮ ሃያ አንደኛዉን የጀርመንን የዉህደት ቀን ብቻ ሳይሆን የምትገኝበትን የኖርዝራይን ዊስፋልያ ግዛት በፊድራልነት የተመሰረተችበትን ስድሳ አምስተኛ አመትንም ነዉ በድርብ በአል ያከበረችዉ። በቦን ከተካሄደዉ ከሶስት ቀኑ ፊስታ በኋላ እንደተገለጸዉ በበአሉ ላይ ሰባት መቶ ሃምሳ ሽ ያህል እድምተኞች ተገኝተዋል።
ቦን ከተማ በአለም ታዋቂ የሆነዉ እና በተለይ በረቂቅ ሙዚቃ ድርሰቱ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት የLudwig van Beethovennየትዉልድ ስፍራም በመሆንዋ የሱን የሙዚቃ ድርሰት የሚጫወቱ የሙዚቃ ባንዶች እንዲሁ መደባቸዉን ይዘዉ ከቀኑ ጥሩ የአየር ሁኔታ ጋር ሙዚቃዉን ሲያንቆሮቁሩት ነበር። ቬትሆፈን የትዉልድ ቦታ እና ያደገበትንም ቤት ለማየት በዚህ አጋጣሚ

Flash-Galerie Tag der deutschen Einheit in Bonn

ወደ ቦን የመጣዉ የቱሪስት ብዛት የረቂቅ ሙዚቃ አፍቃሪን መገመት አያዳግትም።
ጀርመን ዘንድሮ ቦን ከተማ ላይ ያከበረችዉን ሃያ አንደኛዉን የዉህደት በአል ላይ ኢትዮያዉያንን የማግኘት እድል ግን አላጋጠመኝም። ለነገሩ ቦን ከተማ በቆዳ ስፍት የአዲስ አበባን ሩብ ብትሆንም ፣ ሶስመቶ ሃያ አምስት ሽ ነዋሪን ያቀፈች እና በአቀረበችዉ ድግስ ከሰባት መቶ ሽ በላይ እድምተኛን ያስተናገደች በመሆንዋ ከዝያ ዉስጥ ኢትዮጽያዊን ማግኘቱ ትንሽ ያዳግታል፣ ቢሆንም በቅርቡ ከኢትዮጽያ በቦን ዪንቨርስቲ የከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል የመጡ ኢትዮጽያዉያን በበአሉ ላይ ተገኝተዉ ነበር አነጋግረናቸዋል።
በበአሉ ላይ ከአስራ ስድስቱ የጀርመን ግዛቶች አቅርበዉ ጥሩ የተባለ ትርኢን ያቀረበዉ ይሄ ግዛት ነዉ ባይባልም ዘንድሮ ነጻናት አንድነት ደስታ በሚል መርሆ ፊስታን ያዘጋጀችዉ የኖርዝ ራይን ዊስት ፋልያ ግዛት በተለይም ራድዮ ጣብያችን የሚገኝበት የቦን ከተማ እንግዶችዋን አስተናግዳ በመሸኝትዋ ቀደምቱን ቦታ የያዘች ይመስለናል። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!


አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic