የጀርመን ፕሬዚዳንት ጋውክ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 20.03.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን ፕሬዚዳንት ጋውክ

በትናንቱ ዕለት በጀርመን ምክር ቤት በተካሄደ የድምፅ አሰጣጥ ሥርዓት በከፍተኛ ድምፅ የተመረጡት አዲሱ የጀርመን ፕሬዚደንት ዮአኺም ጋውክ የፕሬዚደንትነቱን ሥልጣን የመያዛቸው ምልክት የሆነውን በበርሊን የሚገኘውን የሽሎስ ቤልቪው ቤተመንግሥት ቁልፍ

በትናንቱ ዕለት በጀርመን ምክር ቤት በተካሄደ የድምፅ አሰጣጥ ሥርዓት በከፍተኛ ድምፅ የተመረጡት አዲሱ የጀርመን ፕሬዚደንት ዮአኺም ጋውክ የፕሬዚደንትነቱን ሥልጣን የመያዛቸው ምልክት የሆነውን በበርሊን የሚገኘውን የሽሎስ ቤልቪው ቤተመንግሥት ቁልፍ ባለፉት ሣምንታት የፕሬዚደንትነቱን ሥልጣን በተጠባባቂነት ይዘው ከቆዩት የክፍላተ ሀገር ውክልና ምክር ቤት ወቅታዊ ፕሬዚደንት የባየር ክፍለሀገር ጠቅላይ ሚንስትር ሆርስት ዜሆፈር ዛሬ በይፋ ተረከቡ። በዚሁ ሥነ ሥርዓት ወቅት የቀድሞው ፕሬዚደንት ክርስትያን ቩልፍም ተገኝተው ለጋውክ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጀርመን በትናንትናው ዕለት አዲስ የፌደራል ሬፑብሊክ ፕሬዚደንት መርጣለች። 80 ከመቶ ያክል ድምፅ በማግኘት የቀድሞው የፕሮቴስታንት ቄስና የምሥራቅ ጀርመን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ዮአሂም ጋውክ 11ኛው የጀርመን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል። ጋውክ ከተመረጡ በኃላ ባደረጉት ንግግር ለአገሪቷ የወደፊት እጣ ህዝቡ ምን ያህል ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልፀዋል። የጀርመን መህራይተ መንግስተ አንጌላ ሜርክል ምንም እንኳን የጋውክ ደጋፊ ባይሆኑም በውጤት ደስተኛ ናቸው። « አዎ! ክቡር ፕሬዚዳንት፤ ምርጫውን ተቀብያለሁ። » ሲሉ ነበር ዮአሂምጋውክ - ለፌደራል ጀርመን የህዝብ ተወካዮች- ቡንደስታግ ፕሬዚዳንት ኖርበርት ላምቤርት እና ለሸንጎው አባላት የጀርመን ፕሬዚደንት ሆነው መመረጣቸውን በስምምነት ያረጋገጡት።

የ72 ዓመቱ ጋውክበርሊን በሚገኘውፓርላማበተካሄደውፌደራላዊሸንጎ80 ከመቶ በላይ ድምፅ በማግኘት በመጀመሪያ ዙር ምርጫ አሸናፊ ሆነዋል። የጋውክ ማሸነፍ ለማንም አስገራሚ ዜና አልነበረም። ምክንያቱም ጋውክለምርጫየቀረቡትአምስት የአገሪቷ ፓርቲዎችን ወክለው ነውና። ይኼውም የክርስቲያን ዲሚክራቲክ እና ሶሻል ህብረት፣ ሶሻልዲሚክራቶች ፓርቲ፣የነጻዴሞክራቶች ፓርቲናየአረንጓዴውፓርቲየጋራዕጩሆነውነው የቀረቡት። ጋውክ በስልጣን ዘመናቸው መሪዎች እና ህዝቡ እንዲቀራረቡ የበኩላቸውን እንደሚጥሩ ተናግረዋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ህዝቡ ኃላፊነት መውሰድ እንደሚገባው አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

« ኃላፊነት ወሰድንም አልወሰድንም! ይህ ሀገራችን ነው። ልንገነዘበው የሚገባን ነገር አለ። በንቃት የምትሳተፉትም ሆነ ዳር ላይ የቆማችሁት፤ ሁላችሁም ልጆች አሏችሁ። ለእነሱ ነው ይህንን አገር የምናስረክባቸው። ወደፊት ልጆቹ ይህን ሀገር፤ ሀገራችን ብለው እንዲጠሩ የኛን ጥረት ይጠይቃል። »

በጀርመን ፊደራላዊ ምክር ቤት- ቡንደስታግ ከፍ ያለ ጭብጨባ ብቻ ሳይሆን የተሰማው በርካታ ፈገግታ የተሞሉ ፊቶችም ታይተዋል። የጋውክ መሰረት የቀድሞው ምስራቅ ጀርመን ነው። ምዕራብ እና ምስራቅ ጀርመን ከተዋሀዱ በኋላ አንድ ምስራቅ ጀርመናዊ ተወላጅ ፕሬዚዳንት ሲሆን ጋውክ የመጀመሪያ ናቸው። እንደ ጋውክ ሁሉ የጀርመን መህራይተ መንግስቷ አንጌላ ሜርክል የበፊቷ ምስራቅ ጀርመን ተወላጅ ናቸው። ሜርክል እንደተናገሩት ጋውክ የሚመኙት እጩ ተወዳዳሪ አልነበሩም።ይሁንና አሉ ሜርክል

«ይሁንና ደስተኛ ነኝ። ውጤቱም አሳማኝ ነው!ለነገሩ በሂደት የክርስቲያን ዲሞክራቶች እና የክርስትያን ሶሻልህብረት ፓርቲዎች ተወያይተን ዮአሂምጋውክ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ስማምተንበታል። ዛሬ እራሳቸውን ባስተዋወቀበት የመክፈቻ ንግግራቸውም፤ ለፕሬዚደንትነት ብቁ እና የህዝቡን ፍላጎት በደንብ የሚገነዘቡ እንደሆኑ ለማየት ተችሏል። የዛኑ ያህል ብዙ ፖለቲከኞች ለአገሪቱ የሚያደርጉትን ይረዳሉ ከግምት ውስጥ ያስገባሉ። ስለሆነም በጥሩ ሁኔታ ተባብረን እንሰራለን ብዬ አምናለሁ።»

Der neue Bundespräsident Joachim Gauck (2.v.l) bekommt am Sonntag (18.03.2012) Blumen von Bundeskanzlerin Angela Merkel (CDU) nach seiner Wahl durch die Bundesversammlung im Reichstag in Berlin. 1240 Wahlleute bestimmten den neuen Bundespräsidenten. Foto: Kay Nietfeld dpa +++(c) dpa - Bildfunk+++

ፕሬዚዳንት ዮአሂም ጋውክ እና የጀርመን መህራይተ መንግስተ አንጌላ ሜርክል

ሜርክል በዕለት ተዕለት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሂደት ከአዲሱ ፕሬዚደንት ሀሳብ ቢያቀርቡላቸው ደስተኛ እንደሚሆኑ ገልፀው፤ አልፎ አልፎ የሀሳብ አለመግባባት ሊኖር ቢችልም በንግግር መፍታት ይቻላል ብለዋል። የስራ ኃላፊነታቸውን በተመለከተ ሜርክል ሲመልሱ፤ « የፊደራል ፕሬዚደንቱን የሚመለከቱ ነገሮች ውስጥ ጣልቃ አልገባም። የራሳቸው ውሳኔዎች ናቸው። »

ጋውክ እንዳለፉት ሁለት የጀርመን ፕሬዚዳንቶች በምክንያት ከስራቸው ካልተሰናበቱ ፤ህጉ 5 አመት የስልጣን ዘመን ይፈቅድላቸዋል። አዲሱ የጀርመን ፕሬዚዳንት ጋውክ በሚመጣው አርብ ቃለ መሀላ በመፈጸም ስልጣኑን ይረከባሉ።

ካይ አሌግዛንደር ሾልስ

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 20.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14Mwg
 • ቀን 20.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14Mwg