የጀርመን ጥምር መንግሥት ምሥረታ ሂደት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 01.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን ጥምር መንግሥት ምሥረታ ሂደት

መስከረም 12 2006 ዓም የጀርመን ምክር ቤት ምርጫ ተካሂደ አሸናፊውና ተሸናፊው ቢለይም እስካሁን ግን አዲስ መንግሥት አልተመሰረተም ። አሸናፊዎቹ እህትማማቾቹ የክርስቲያን ዲሞክራት ህብረት ና የክርስቲያን ሶሻል ህብረት ፓርቲዎች አሁንም ተጣማሪ ፓርቲ ፍለጋ ላይ ናቸው ።

ከ 10 ቀናት በፊት የተካሄደው የጀርመን ምክር ቤት አባላት ምርጫ በእህትማማቾቹ የክርስቲያን ዲሞክራት ሕብረት ፓርቲ በጀርመንኛው ምህፃር CDU ና በክርስቲያን ሶሻል ህብረት ፓርቲ CSU አሸናፊነት ቢጠናቀቅም የመንግስት ምሥረታው ግን ገና በሂደት ላይ ነው ። ሁለቱ ወግ አጥባቂ ፓርቲዎች በአጠቃላይ ያገኙት 41.5 በመቶ ድምፅ ለብቻው መንግሥት ለመመስረት የሚያበቃ ባለመሆኑ የግድ ተጣማሪ ያስፈልጋቸዋል ። የሥልጣን ዘመኑን ባጠናቀቀው የጀርመን መንግሥት ከ CDU ጋር ተጣምረው ይገዙ የነበሩት የነፃ ዲሞክራቶቹ ፓርቲ ተሸንፈው ከምክር ቤት መውጣት CDU ና CSU ን በ 2 ተኛ ደረጃ ድምፅ ካገኙት ከ ሶሻል ዲሞክራቶች አለያም አራተኛ ደረጃ ድምፅ ካገኙት ከአረንጓዴዎቹ ጋር የመጣመር አማራጭ ብቻ ትቶላቸዋል ። ሆኖም የጥምር መንግሥት ምሥረታው እንደተፈለገው የተፋጠነ አልሆነም ። ሂደቱ ምን ይመስላል ? ምንስ ይጠበቃል ? የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርና የህግ ባለሞያ የሆኑትን ዶክተር ለማ ይፍራሸዋን ጠይቀናል ። ዶክተር ለማ በቅድሚያ በጀርመን ጥምር መንግስት የሚመሰረትበትን ምክንያትና ችግሮቹን ያስረዱናል ።

በዚሁ መሠረት በመራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የሚመሩት ወግ አጥባቂዎቹ የመሃል ግራ ፖለቲካ ከሚያራምዱት ከሻል ዲሞክራቶች ጋር ለመጣመር የሚያስችላቸውን ንግግር የፊታችን አርብ ይጀምራሉ ። የነዚህን ታላላቅ ፓርቲዎች ጥምረትም ብዙ ደጋፊ አለው ። የንግግሩ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ መገመት ቢያዳግትም ዶክተር ለማ ግን ፓርቲዎቹ መጣመራቸው አይቀርም የሚል እምነት አላቸው ። ምክንያታቸውን ያስረዳሉ ።CDU CSU ና SPD ከጥቂት ቀናት በኋላ የሚጀምሩት የመጀመሪያ ዙር ንግግር ነው ። በዚህ ንግግር በዋነኛነት የሚነሱ የመነጋገሪያ ነጥቦችስ ምንድን ናቸው ? ዶክተር ለማ በዶክተር ለማ አስተያየት ሶሻል ዲሞክራቶች ከወግ አጥባቂዎቹ ጋር መጣመራቸው የኋላ የኋላ በራሳቸው ላይ ችግር ማስከተሉ አይቀርም ። ይህንኑ መዘዝ በመፍራትም ይመስላል ለመጣመር ከመስማማቱ በፊት አባላቱ በሙሉ ድምፅ እንዲሰጡበት እንደሚያደርግ ባለፈው ሳምንት አስታውቋል ። አርብ ከ SPD ጋር ንግግር የሚጀምሩት ወግ አጥባቂዎቹ በመጪው ሳምንት ከአረንጓዴዎቹ ጋርም የመጀመሪያ ዙር ንግግር እንደሚያካሂዱ አስታውቀዋል ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic