የጀርመን የፖለቲካ ፓርቲዎች ድጎማና ዉዝግቡ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 19.01.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን የፖለቲካ ፓርቲዎች ድጎማና ዉዝግቡ

ተቃዋሚዎች እንደሚሉት FDP በተለይ ለሆቴሎች የግብር ቅናሽ እንዲደረግ አጥብቆ መከራከሩ ምናልባት የደጓሚዎቹን ዉለታ ለመመለስ ሳይሆን አልቀረም

default

የFDP መሪና የጀርመን ዉጉሚ

በምዕራቡ አለም ግለሰቦችና ኩባንዮች ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጡት የገንዘብ ድጎማ ወይም ርዳታ አንዳዴ ዉል እየሳተ የሐገርንና የመንግሥትን ሥራ እና አሠራር ያዛባዋል።ይሕ ቢቀር ገንዘብ ተቀባዩን የፖለቲካ ፓርቲና ፖለቲከኞቹን ለጉቦኝነትና ለሙስኝነት ጥርጣሬ ይዳርጋል።እዚሕ ጀርመን ዉስጥ በቅርቡ ተጣማሪ መንግሥት ከመሰረቱት የፖለቲካ ፓርቲዎች መካካል የሊብራል ዲሞክራቶቹ ፓርቲ FDP ከአንድ የሆቴሎች ኩባንያ ከአንድ ሚሊዮን ዩሮ በላይ ድጎማ መቀበሉ የሐገሪቱን ፖለቲከኞች እያወዛገበ ነዉ።ተቃዋሚዎች እንደሚሉት FDP በተለይ ለሆቴሎች የግብር ቅናሽ እንዲደረግ አጥብቆ መከራከሩ ምናልባት የደጓሚዎቹን ዉለታ ለመመለስ ሳይሆን አልቀረም።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለሚካኤል ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

Yilma Hinz

Negash Mohammed

Hirut Melesse

Audios and videos on the topic