የጀርመን የጦር መሣሪያ ለኩርዶች | ዓለም | DW | 01.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የጀርመን የጦር መሣሪያ ለኩርዶች

ኢራቅ ዉስጥ ለሚገኙ የኩርድ ተወላጆች የጦር መሣሪያ እናቅርብ የሚለዉ ሃሳብ ባለፉት ሳምንታት እዚህ ጀርመን ሲነሳ ሁለት የተለያዩና የሚፃረሩ አስተያየቶች ባለፉት ቀናት ተሰምተዋል። በእነዚህ ነጥቦች ላይም ሰሞኑን ፖለቲከኞቹ ሲከራከሩበት ሰንብተዋል።

አንደኛዉ ወገን ኩርዶችን በጀርመን የጦር መሣሪያ ማስታጠቅ አደጋ አለዉ ሲል ሌላዉ ወገን በበኩሉ እነሱን ማስታጠቅ በመካከለኛዉ ምሥራቅ የእስልምና መንግሥታትን እንመሠርታለን የሚሉትን ሽብር ፈጣሪዎች እዚያዉ እንዋጋለን የሚለዉን ምላሽ ሰጥቷል። የጀርመን የጣምራ መንግሥትም በዚሁ የጦር መሣሪያ ለኩርዶች እንስጥ በሚለዉ ሃሳብ ተስማቷል። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic