የጀርመን የዉህደት ቀን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 03.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን የዉህደት ቀን

22ኛዉ የጀርመን የዉህደት ቀን መታሰቢያ በዓል ዛሬ በመላ ሀገሪቱ ተከብሮ ዉሏል። የዘንድሮዉ በዓል በይፋዊ ደረጃ ፕሬዝደንት ዮአኺም ጋዉክና መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በተገኙበት በሙኒክ ከተማ ነዉ ደምቆ የተከበረዉ። ምስራቅና ምዕራብ ጀርመን የተዋሃዱበት 22 ተኛ አመት ዛሬ በመላ ጀርመን ተከብሮ ዋለ ።


በስነ ስርዓቱ ላይ የጀርመን ፕሬዝዳንት ዮአሂም ጋውክና መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እንዲሁም ከ1500 የሚበልጡ ባለሥልጣናትና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል። በአሉን ያስተናገደው የባየር ፌደራዊ ክፍለ ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትር ኽርስት ዜሆፈር በስነ ስርዓቱ ላይ ባሰሙት ንግግር ውህደቱ እንዲሳካ ምክንያት የሆኑትን ሰዎች አመስግነዋል።


« የአንድነትና የነፃነቱን መንገድ የጠረገው በጀርመን ሶሻሊስት አንድነት ፓርቲ ላይ በግልፅ የተካሄደው አመፅ ነው ። ለነዚህ ሰዎች ትልቅ ምስጋና ማቅረብ ይገባናል ብዮ አስባለሁ ። እነዚህን ቁርጠኛ ሰዎች እግዚአብሄር ይባርክ !»
በሌላ በኩል ከዛሬ 15 አመት አንስቶ ሲደረግ እንደቆየው በዛሬው እለትም ጀርመን ውስጥ የሚገኙ ከ 600 መቶ በላይ መስጊዶች ለጎብኚዎች ክፍት ሆነው ውለዋል ። ዘንድሮ ትኩረቱ የእስልምና ስነጥበብና ባህል የሚል ነው ።

በተለያዩ የጀርመን ከተሞችም በተለያዩ ዝግጅቶች በዓሉ የተከበረ ሲሆን በሙኒክ ከተማ ከ1,500 በላይ ከፍተኛ ባለስልጣናትና እንግዶች መገኘታቸዉ ተገልጿል። የምዕራብና ምስራቅ ጀርመን ዉህደት ያመጣቸዉ ለዉጦች መኖራቸዉ እንዳለ ሆኖ በኤኮኖሚዉ ረገድ በህዝቡ ዘንድ አሁንም አለመርካት እንደሌለ ነዉ የሚነገረዉ። ይህንና ተያያዥ ጥያቄዎችን በማንሳት የበርሊኑ ወኪላችን ይላማ ኃይለሚካኤልን ስለበዓሉ አከባበር በስልክ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ አነጋግሬዋለሁ፤

ይላማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic