የጀርመን የአፍሪቃ ፖሊሲ | ኢትዮጵያ | DW | 11.02.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጀርመን የአፍሪቃ ፖሊሲ

የጀርመኑ የልማት ትብብር ሚኒስቴር ጌርድ ሙለር ባለፈዉ ዓርብ በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ መንግስትና ከአፍሪቃ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት አፍሪቃ በሀገራቸው የውጭ ፖሊሲ ላይ ትልቅ ትኩረት ማግኘቷን አስታወቁ። ሚንስትሩ እንዳስረዱት፣

ጀርመን ከሁለት ዓመት በፊት ከአፍሪቃ ጋ የምታደርገውን ትብብር ማጠናከር የሚያስችላት አዲስ የአፍሪቃ ፖሊሲ ነድፋለች። ከአህጉሪቱ ጋር ያለዉን የጀርመንን ትብብር ግንኙነት በተመለከተ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ የጀርመኑን የልማት ትብብር ሚኒስትር ጌርድ ሙለርን አነጋግሮአቸዉ ነበር።

የጀርመኑ የልማት ትብብር ሚኒስቴር ጌርድ ሙለር ባለፈዉ አርብ በአዲስ አበባ ባደረጉት ጉብኝት ከኢትዮጵያ መንግስትና ከአፍሪቃ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል። ጌርድ ሙለር የጀርመን የልማት ትብብርና የጀርመን የአፍሪቃ ፖሊሲን በተመለከተ እንደገለፁት ጀርመን በአፍሪቃ ያላትን የንግድ አማራጭ፤ በአህጉሪቱ እስካሁን ፤ እንብዛም ትኩረት አልተሰጠዉም። በልማት ፖሊሲ፤ በግል የንግድ ዘርፍ እንዲሁም በምግብ ዋስትና ረገድ የጀርመን የልማት ትብብር ሚኒስቴር የሚያደርገዉ እንቅስቃሴ እንዴት ያገናዝቡታል ለሚለዉ ጥያቄ የጀርመኑ የልማት ትብብር ሚኒስትር ጌርድ ሙለር ሲመልሱ፤ « በጀርመን የልማት ትብብር ላይ የትኩረት አቅጣጫ ነች። አፍሪቃ ለኛ ትልቅ እድል የያዘትች ልዩ አህጉር ናት። ስለዚህም ይህንን ለጀርመንና ለአዉሮጳ ጠቅላላ ግልፅ ማድረግ ያለብን፤ 100 ግዜ ከጀርመን እንደምትበልጥና፤ እጅግ ከፍተኛ እምቅ ጉልበት ያላት፤ በሚቀጥሉት 30-50 ዓመታት ዉስጥ በእጥፍ እንደምታድግና ፤ በዚህም ብቻ ሳይሆን በሌሎች የቆዩ ግንኙነታችን የተነሳ ወደፊት ከአፍሪቃ ጋር ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደምንሰራ እገልጻለሁ»

Flash-Galerie Der Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Äthiopien

የጀርመን ፖሲሲ ካለፉ ጥቂት ግዝያት ወዲህ በአፍሪቃ የጥሪ ሀብት ለዉጭና በመከላከያዉም ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶታል። ይኸዉ ትኩረቱ ምናልባት በአፍሪቃ ዘላቂ ግንኙነት ለመፍጠር እና ቻይና ህንድ በአህጉሩ ከጀመሩት ታታሪነት ጋር ለመፎካከር ሊረዳት እንደሚችል የጀርመኑ ልማት ሚኒስትር ጌርድ ሙለር ገልጸዋል፤ « የአዉሮጳ ህብረት ጀርመን አብረዉት በመተባበር የሚሰሩት የአፍሪቃ ህብረት ዋንኛዉ የአፍሪቃ ተቋማት ማዕከላዊ አስተባባሪ አካል ነዉ። በዚህ ትብብራችን ለኢኮኖሚዉ ጥያቄዎች እና ለመልካም አስተዳደር ልዩ ትኩረት እንሰጣለን። በዚህም ላይ የአፍሪቃ ህብረት ዋንኛዉ የትብብር ማዕከል ሆኖ ይቆያል»

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic