የጀርመን የነጻ ትምህርት እድል | ኢትዮጵያ | DW | 25.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጀርመን የነጻ ትምህርት እድል

የጀርመን መንግሥት በሦስት የአፍሪቃ ሃገራት በመሬት አስተዳደርና ፖሊሲ ትምህርት የሦስተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር የነፃ ትምህርት እድል እንደሚሰጥ አስታወቀ ።

ባለፈዉ ሃሙስ አዲስ አበባ ዉስጥ በተካሄደዉ ሥነ-ስርዓት ላይ፤ በኢትዮጵያ በባሕርዳር ዩንቨርስቲ እንዲሁም በናሚቢያና ታንዛንያ በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች በሚሰጡ የ «ፒ ኤች ዲ» ፕሮግራሞች አንድ መቶ አፍሪቃዉያን ተጠቃሚዎች እንደሚሆኑ ተነግሮአል። በዚህ መድረክ ላይ ተገኝተዉ የነፃ ትምህርት እድሉን ይፋ ያደረጉት የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና የልማት ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ቶማስ ሲልበርሆርን በሦስቱ ሃገራት ዩንቨርስቲዎች ለዶክትሪት ዲግሪያቸው ለሚማሩ አፍሪቃዉያን የትምህርትና የቀለብ ሙሉ ወጫቸዉን የሚችለዉ የጀርመን መንግሥት እንደሚሆንም አስታውቀዋል። ዝግጅቱ ላይ የተገኘዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮኃንስ ገብረግዚአብሄር ዘገባዉን ልኮልናል።

ዮኃንስ ገብረግዚአብሄር

አዜብ ታደሰ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic