የጀርመን የምጣኔ ሐብት ድቀትና የሐገሪቱ ባንክ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 29.04.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን የምጣኔ ሐብት ድቀትና የሐገሪቱ ባንክ

በ2008 1.2 ቢሊዮን ዮሮ ከስሮ የነበረዉ ዶቼ ባንክ ዘንድሮ ኪሳራዉን ተቋቋሙ አትራፊ መሆኑ ለገንዘብና ለምጣኔ ሐብት ተንታኞች አስደናቂ ነዉ-የሆነዉ

default

የዶቼ ባንክ ሕንፃ

የገንዘብ ተቋማት ክስረትና የሐገራት ምጣኔ ሐብት ድቀት ዜና በደመቀበት ባሁኑ ወቅት ከወደ ፍራንክ ፈርት ቢያንስ ለጀርመን ትንሽ ግን የምሥራች ብጤ ተስፋ ተሰምቷል።የጀርመን ብሔራዊ ባንክ Deutsche Bank አራተኛ ወሩን ባገመሰዉ በአዉሮጳዉያኑ ሁለት ሺሕ ዘጠኝ አንድ ሚሊዮን ዩሮ አትርፏል።በ2008 1.2 ቢሊዮን ዮሮ ከስሮ የነበረዉ ዶቼ ባንክ ዘንድሮ ኪሳራዉን ተቋቋሙ አትራፊ መሆኑ ለገንዘብና ለምጣኔ ሐብት ተንታኞች አስደናቂ ነዉ-የሆነዉ።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል እንደዘገበዉ ሜርሴዲስ ቤንሰን የመሳሰሉ የጀርመን ትላልቅ የመኪና ኢንዱስትሪዎች ግን ገበያ አጣን-ከሰርንም እንዳሉ ነዉ።