የጀርመን የምርጫ ዝግጅት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 07.09.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

 የጀርመን የምርጫ ዝግጅት

ጀርመን ዉስጥ በመጪዉ መስከረም 16 ለሚደረገዉ አጠቃላይ ምርጫ የሚወዳደሩ ፖለቲከኞች የምረጡኝ ዘመቻ፣መራጩም ይስማማኛል የሚለዉን ዕጩ የመለየቱ ሒደት እየተጠናከረ ነዉ።አንዳድ መራጮችም የሐገሪቱ የምርጫ ሕግ በሚፈቅደዉ መሠረት ድምፃቸዉን በፖስታ እየሰጡ ነዉ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:33

የጀርመን የምርጫ ዝግጅትና የአፍሪቃ ጋዜጠኞች ቅኝት

                         

ጀርመን ዉስጥ በመጪዉ መስከረም 16 ለሚደረገዉ አጠቃላይ ምርጫ የሚወዳደሩ ፖለቲከኞች የምረጡኝ ዘመቻ፣መራጩም ይስማማኛል የሚለዉን ዕጩ የመለየቱ ሒደት እየተጠናከረ ነዉ።አንዳድ መራጮችም የሐገሪቱ የምርጫ ሕግ በሚፈቅደዉ መሠረት ድምፃቸዉን በፖስታ እየሰጡ ነዉ።የዶቸ ቬለ የአፍሪቃ ቋንቋዎች ማስተባበሪያ፣ በተለያዩ ከተሞችና አካባቢዎች የሚደረገዉን የምርጫ ዝግጅትና ሒደት የሚከታተል የጋዜጠኞች ቡድን ባለፈዉ ዕሁድ ከቦን አሰማርቷል።ከስድስቱ የቋንቋ አገልግሎቶች ከተወከሉት ጋዜጠኞች አንዷ ኂሩት መለሰ ናት።በዛሬዉ አዉሮጳና ጀርመን ዝግጅት የጋዜጠኞቹ ቡድን እስከዛሬ ጠዋት ድረስ የታዘበዉን በተመለከተ ነጋሽ መሐመድና ኂሩት መለሰ ያደረጉትን አጭር ጥያቄና መልስ እናቀርብላችኋለን። 

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ
 

Audios and videos on the topic