የጀርመን የምርጫ አካሄድና አስተምህሮቱ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 27.08.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን የምርጫ አካሄድና አስተምህሮቱ

የፊታችን መስከረም ለሚካሄደው የጀርመን አጠቃላይ ምርጫ የሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ዘመቻ ላይ ናቸው። ፓርቲዎቹ ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ ይረዳል ባሉት መንገድ የመራጩን ህዝብ ቀለብ ለመሳብ እየጣሩ ነው።

መስከረም 12 ፣ 2006 በጎርጎሮሳውያኑ መስከረም 22 2013 ዓም በጀርመን አጠቃላይ ምርጫ ይካሄዳል ። ከአንድ ወር ያነሰ ጊዜ በቀረው በዚህ ምርጫ የሚሳተፉ ከ 30 የሚበልጡ እውቅና ያገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሚቀጥሉት 4 ዓመታት እናከናውናለን የሚሉትን መርሃ ግብራቸውን እያስተዋወቁ ነው ። በአሁኑ ሰዓትም በዋነኞቹ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የቃላት ጦርነቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል ። ለረዥም ጊዜ ጀርመን የኖሩትና እዚሁ ጀርመን የተማሩት የህግ ባለሞያና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ዶክተር ለማ ይፍራ ሸዋ እንዳሉት ምንም እንኳን ከ30 በላይ ፓርቲዎች ለውድድር ቢቀርቡም አሸንፈው

Angela Merkels Wahlkampfauftritt am Samstag 24. August 2013 in Bonn

አንጌላ ሜርክል

በጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መቀመጫ ሊያገኙ የሚችሉት ከ6 ወይ ከ 7 አይበልጡም ። ዶክተር ለማ እንደዘረዘሩት እነዚህን ፓርቲዎች በአሁኑ የምርጫ ዘመቻ የሚያከራክሯቸው ወሳኝ የሚባሉ ጉዳዮች 6 ናቸው ።በምርጫ ዘመቻቸው ከነዚህ ወሳኝ የመከራከሪያ ርዕሶች የተለዩ ሃሳቦችን የሚያነሱ ፓርቲዎችም አሉ ።ከዋነኛዎቹ የጀርመን የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመራሄ መንግሥትነት የሚወዳደሩት የሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ እጩ የቀድሞው የገንዘብ ሚኒስትር ፔር ሽታይንብሩክና የክርስቲያን ዲሞክራት ህብረት ፓርቲ እጩ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የምርጫ ዘመቻውን በሰፊው ተያይዘውታል ። የፊታችን እሁድ ደግሞ ፊት ለፊት የቴሌቪዥን ክርክር ያካሂዳሉ ። ፔር ሽታይን ብሩክ ከአሁኑ በቀደመው የጀርመን ጥምር መንግሥት በአንጌላ ሜርክል ካቢኔ የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ያከበተ ልምድ ያላቸው የፖለቲከኛ ናቸው ።

SPD-Kanzlerkandidat Peer Steinbrück

ፔር ሽታይንብሩክ


ጀርመን በዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ቀውስ ሳትጎዳ እንድታልፍ በማድረግ የሚመሰገኑት ለ 3ተኛ የሥልጣን ዘመን የሚወዳደሩት የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ እጩ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በህዝብ አስተያየት መመዘኛ መሠረት ተቀናቃናቸውን የሶሻል ዲሞክራቶቹን ፓርቲ እጩ ፔር ሽታይንብሩክን ለወራት በ 30 ነጥብ ሲመሩ ቆይተዋል ። ይሁንና አሁንም የመጨረሻ መፍትሄ ያልተበጀለት የግሪክ የገንዘብ ቀውስ ሜርክልን ችግር ውስጥ ሊጥል እንደሚችል እየተነገረ ነው ።
ዶክተር ለማ የጀርመን የምርጫ ዝግጅትና አካሄድ ዲሞክራሲን ተግባራዊ እናደርጋለን ለሚሉ አዳጊ አገሮች አርአያነቱ የጎላ መሆኑን ይናገራሉ ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic