የጀርመን የልማት ተራድዖ ፖለቲካ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 18.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን የልማት ተራድዖ ፖለቲካ

ባለፉት 4 ዓመታት የጀመን የልማት ተራድዖ ሚንስትር በመሆን ሥልጣን ላይ የሚገኙት ዲርክ ኒበል፤ እንዲሁ በዛ ያለ ገንዘብ መስጠት ጥሩ ልማት ነክ ፖለቲካ አይደለም ሲሉ በርሊን ውስጥ ትናንት በቀረበ ዘገባ ላይ አያይዘው ተናግረዋል። ኢትዮጵያን የመሳሰሉ

አዳጊ አገሮች ከእንግዲህ ያላንዳች ቅድመ ግዴታ ፣ የበጀት ድጎማ አያገኙም ሲሉም ሚንስትሩ ጠቁመዋል።

ጀርመን ባለፉት ጥቂት ዓመታት የልማት ተራድዖ በጀትን በመቀነስ ላይ ስትሆን፤ ዘንድሮ የ 2013 ጎርጎሪዮሳዊው ዓመት በጀት 87 ሚሊዮን ዩውሮ ተቀንስሎት፣ በ 6,3 ቢሊዮን ዩውሮ ገደማ ተወስኗል። በጀቱ ቢቀነስም፤ ለዘብተኛ የፖለቲካ ፈለግ የሚከተለው ፓርቲ (FDP) አባል ዲርክ ኒበል፣ እንደርሳቸው ግምት አዎንታዊ ሂደት የታየበትን ተግባራቸውን ዋጋ ማሳጣት አይቻልም። ስለጀርመን የልማት ተራድዖ ሚንስቴር ይዞታና የወደፊት የሥራ እንቅሥቃሤ፤ የዶይቸ ቨለ ባልደረባ ማርሴል ፉዑርስተናው አንድ ዘገባ አሰናድቷል፤ ጥንቅሩ ተከታዩን ይመስላል።

ጀርመን GIZ በሚል የጀርመንኛ ምህጻር በታወቀው ሥራ አስፈጻሚቡድኗ በኩል ፣ በዓለም ዙሪያ በልማት ውጥንና አፈጻጸም ረገድ ማለፊያ ሥም ነው ያተረፈችው ። ዋናው የልማት ተራድዖው መ/ቤት 2 ቢሊዮን ዩውሮ የተመደበለት ሲሆን፤ ¾ኛውን በቀጥታ የኒበል መ/ቤት ነው እንደአስፈላጊነቱ የሚያውለው። ቀሪውን የጀርመን ዓለም አቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት(GIZ)ነው የሚያካሂደው። ሌሎች እርዳታ ለጋሽ መንግሥታትም ሆኑ ድርጅቶች፣ ለልማት ተራድዖ የሚሰጡትንም የሥራ ኮንትራት አያይዞ ነው የሚያከናውነው።

ጀርመን በአሁኑ ጊዜ፣ ለአዳጊ አገሮች የበጀት እርዳታ ለማቅረብ፤ ከምንጊዜውም በበለጠ፤ የሰብአዊ መብት መጠበቅን ቅድመ ግዴታ አድርጋ ነው የማታቀርበው። ለምሳሌ ዩጋንዳ ፤ ግብረ ሰዶማውያንን በሞት እንዲቀጡ ለማድረግ መሻቷን በገለጸችበት ጊዜ፣ ከጀርመን የበጀት እርዳታ ወዲያውኑ ነበረ የተቋረጠባት። የጀርመንን አቋም አሁን የአውሮፓው ኅብረትም መጋራቱ እየተነገረ ነው።

1,ቀደም ባለው ጊዜ፣ ከአውሮፓው ኅብረት የበጀት እርዳታ ክፍል ጋር በተደረገ ስምምነት ሳቢያ፣ የጀርመን ቀረጥ ከፋዩ ህዝብ ገንዘብ ፣ የተቃውሞ ፖለቲከኞችን እሥር ቤት ለሚያጉር፤ በጋዜጠኞች ስራ ላይ እገዳ ለሚያደርግ ማንኛውም ታዳጊ ሀገር ተሰጥቶ ይሆናል። በጋራ ስምምነት ረገድ ግን ይህን የሚያደርግ አዳጊ አገር ከጀርመን አንዲት ሳንቲም እንኳ ሊያገኝ አይችልም። በአሁኑ ወቅት ግን ፣ ቅድመ ግዴታን የማያሟላ ማንኛውም ሀገር በፍጹም የበጀት እርዳታ አያገኝም። ይህም የሆነበት ምክንያት፤ የበጀት እርዳታ ለማግኘት ቅድመ ግዴታዎች በመደርደራቸውና ጥብቅ መመዘኛዎች በመቀመጣቸው ነው።»

የጀርመን ሶሺያል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (SPD)የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባልና የኤኮኖሚ ተራድዖ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፣ ሳሻ ራበ ፣ የኒበልን የሥራ ክንዋኔ ከተቀነሰው የልማት እርዳታ ጋር በማያያዝ እንዲህ ሲሉ ነቅፈዋል።

2«እንደምናውቀው፤ አሳፋሪው እጅግ ዝቅተኛው የእርዳታ መጠን ፣ ማለትም 0,38 ከመቶ ፣ በእጥፍ ጨምሮ፣ 10 ቢሊዮን በላይ መድረስ ነበረበት። በሚመጡት 2 ዓመታት

በጀቱ በተጨማሪ እንዲቀነስ ሐሳብ መቅረቡ ራሱ፤ የት ላይ ነው በትክክል ተሠራ የሚባለው ብለን እንድንጠይቅ ይገፋፋናል።»

የጀርመን አረንጓዴ ፓርቲ የልማት ነክ ፖለቲካ ጉዳይ ቃል አቀባይ ዑተ ኮዢ በበኩላቸው፤ የጀርመን የልማት ተራድዖ ሚንስትር የሥራ እንቅሥቃሴ የከሸፈ ነው። ለድሆች ጥብቅና እንደመቆም፣ ሚንስትሩ የጀርመን ኤኮኖሚ አንድ አካል ሆነው ነው ተግባራቸውን የሚያከናውኑት በማ ለት ተችተዋል።

Niebel / Kenia - Kenianer unterschiedlicher Stämme bereiten sich auf eine Theaterszene vor, in der zur Versöhnung zwischen den verfeindeten Ethnien aufgerufen wird. Der deutsche Entwicklungsminister Dirk Niebel hat das von der Gesellschaft für internationale Zusammenarbeit (GIZ) unterstützte Projekt in Karagita im Rift Valley am 19.08.2012 besucht. (Quelle: DW / Marcel Fürstenau)

Kenia Niebel Dirk Niebel Afrika Aussöhnung Theater

የልማት ተራድዖ ሚንስትር ዲርክ ኒበል፣ የተሣሠረ ያሉትን ፣ ማለትም የአርዳታ ድርጅቶችና በወታደራዊ ተልእኮ የተሠማሩ ሚሲዮኖች በፀጥታ አጠባበቅ ረገድ የሚያደርጉትን መተጋጋዝ በመሠረተ ሐሳብ እንደሚደግፉ ነው ያስገነዘቡት። አብዛኞቹ የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የገልለተኛነት አቋማቸውን የሚያዛባ በመሆኑ አይደግፉትም። ኒበል ግን፣ የጀርመን መንግሥት ሰብአዊ ርዳታ ፣ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሥር መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህም ከልማት ተራድዖ ሚንስቴሩ ጋ መታሠሠሩ ትርጉም ያለው ነው። የልማት ተራድዖ የውጭ አመራር አንድ አካል ነው። ይህም ማለት ገልልተኛነት አይታይበትም። ከሀገር ጥቅም አኳያ ነውና የሚመራው---ብለዋል።

«ሰብአዊ እርዳታ ገልለተኛ ነው፣ ገለልተኛም መሆን ይጠበቅበታል።ማንኛውም በጦር ሜዳ የሚቆስል፣ ማበርከት ከሚችሉ እርዳታ ሊያገኝ ይገባል። ይህ ሌሎቹንም ዘርፎች የሚመለከት ነው። የልማት ተራድዖ የውጭ አመራር አንድ አካል ነው። ገለልተኛ አይደለም፣ ከሀጋራዊ ጥቅም አኳያ የሚመራ እንጂ!»።

እስካሁን ጀርመን ፣ የቻይናን የልማት ተራድዖበጥርጣሬ ዐይን ነበረ የምትመለከተው። ሚንስትር ኒበል፤ በተለይ በመንገድ ሥራ ረገድ እንዲሁም በሌሎች መሠረታዊ ልማቶች የቻይና ድርሻ በአዎንታዊ ገጽ የሚታይ ነው፤ ነገር ግን፤ በተፈጥሮ አጠባበቅና በማኅበራዊ ኑሮ ደረጃ ፣ ጉድለት ይታይበታል። በእርዳታ ተቀባዮቹ አገሮች፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል አይሰጥም ሲሉም ኒበል ነቅፈዋል።

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic