የጀርመን የልማት ርዳታና የበጎ ፍቃድ ሠራተኛ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 03.09.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን የልማት ርዳታና የበጎ ፍቃድ ሠራተኛ

እዚያ ስትደርስ እንደ ሁሉም ጎብኚ ደዎሉን ደዉላለች።ከዚያ ከሕንዲዉ ቄስ ፊት ለፊት ስትደርስ እጆችዋን አጣጥፋ ተንበረከከች።ያቺ ወርቃማ-ፀጉር ነጭ ወጣት ያላደገችበን፥ ባሕል-አለሟ-ያልሆነዉን አለም ተቀየጠች።

default

የልማት ርዳታ

የጀርመን የልማት ተራድኦ ሚኒስቴር ዛሬ በጠራዉ ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ለፍትሕና እኩልነት መስፈን የሚታገሉ ከሰወስት ሺሕ በላይ ፖለቲከኞች፥ የምጣኔ ሐብትና የማሕበረሰብ ጉዳይ አዋቂዎችንና ባለሙያዎችን ጋብዟል።ተጋባዦቹ ግን በየመስኩ እዉቅናን ያታረፉ ብቻ አይደሉም።ወጣቶችም ጭምር እንጂ።የቱሪንገንዋ ወጣት የበጎ ፍቃድ የርዳታ ሠራተኛ ከወጣት ተጋባዦቹ አንዷ ናት።ወጣትዋ ሕንድ ዉስጥ ዉስጥ የምታከናዉነዉን ምግባር ተመልክቶ የፃፈዉን ነጋሽ መሐመድ እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።


ዶሪን ግሩትነር-ን እና ሕንዳዊት ባልደረባዋን ሪናን ያሳፈረዉ ባለ-አራት መዘዉር (ፎር ሁዊል) መኪና ወባቁን አየር እየገመሠ-ይከንፋል።የመኪናዉ ጉርምርምታ፥የመንገዱ ግጭግጭታ፥እስከ ገደፉ ከተከፈተዉ ከሾፌሩ ተንቀሳቃሽ ሥልክ-የሚወጣዉ ሙዚቃ፥ አንዱ ከሌላዉ ለመብለጥ-ይመስል በልዩ ረባሽ ጩኸት ይፎካከራሉ።እነ ዶሪን ግን ልብ ያሉት አይመስልም።ምናልባት የሚሔዱበት ቀበሌ ገበሬዎች የአየር ንብረት ለዉጥን መቋቋም የሚችል የአስተራረስ ዜዴ እንዲከተሉ የሚመክሩበትን ብልሐት እያዉጠነጠኑ ሊሆን ችላል።

ዶሪን ግሩትነር የሕንድ ልብሷን አጠለቀች።ደማቅ ወርቃማ ፀጉሯን ከማጅራቷ ጋር ግጥም አድርጋ አሠረችዉ።ከሕንዶች-ጋር ሕንድ አገርነች።ሕንድ-መሰለች።ከሕንዳዊት ጓደኛዋ ጋር ለመንደሪቱ ሕንዶች በእለት ከእለት ኑሯቸዉ የሚጠቅማቸዉን ለማስረዳት ነዉ ጥረቷ።በተለይ ሥለ አየር ንብረት ለወጥ፥ተፈጥሮን ሥለሚጠብቅ የአስተራረስ ዘዴ።ጠቃሚ-አላማ ግን ከባድ ሐላፊነት።

«ማነጋገር ሲጀመር ሥለምን እንደሚነገር መስማት የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች ይሰበሰባሉ።እና ጥያቄ ሲጠየቅ ብዙ ጊዜ የሚመልሰዉ ተጠያቂዉ ለብቻዉ ሳይሆን ተሰብሳቢዉ እንዳለ በቡድን ነዉ።ይሕ በጣም አርኪና ዉጤታማ ሊሆን ይችላል።ግን---ያዉ ሥራችን የሙከራ ነዉ።የሚሆነዉን እያናያለን።»

Entwicklungshilfeminister Dirk Niebel (FDP)

የጀርመን የልማት ተራድኦ ሚኒስቴር አርማና ሚንስትሩ

ዶሪን እና ሪና ከመንደሪቱ (መሐል) ደረሱ።ሕፃናት የያዙ ሴቶች መሬት ላይ ተኮልኩለዋል። ሴቶቹ ከተቀመጡበት አጠገብ ጣዉላ የተደረደረበት ትንሽ ቤት አለች።መደርደሪያዉ በፈንታዉ እቃ በታጨቀባቸዉ የላስቲክ ከረጢቶች ተጨናንቋል።ሱቅ ነች።ዶሪን ከተሰበሰቡት ሴቶች ጋር ማዉራት ጀመረች።ሕንድ ሐገርነች።እንደ ሕንድ ለብሳለች።ናግፑር በነበረችበት ጊዜ ደግሞ ሕንድኛ ተምራለች።በሕንድኛ ታወራ ገባች።
«ይሕ ሱቅ የማነዉ»-ከሴቶቹ ጋር ለመግባቢያ ያለችዉ ጥያቄ-ነበር።የመጀመሪያዉ ግንኙነት ተፈጠረ።ወዲያዉ ካንደኛዋ አስተናጋጅ የሳር ጎጆ ቤት ገብታ ከብዙዎቹ ሴቶች ጋር መሬት ላይ ተቀምጣ-ሻሒዋን ፉት እያለች።ወሬዋን ትሰልቃለች።-ጀርመናዊቷ ወጣት።

ቤተሰበቡ ምን ያሕል ዉሐ እንደሚያገኝ-ጠየቀች።«በቀን-አንድ ሰአት» መልሱላት።እየከፋ የመጣዉ የአየር ንብረት ለዉጥ የብዙዎቹን የማሐራሻትራ ግዛት አካባቢዎች የዉሐ ችግር በሚቀጥሉት አመታት ማባባሱ አይቀርም።ዶሪን የሕንድ የልማት ተራድኦ መስሪያ ቤት የበጎ ፍቃድ ሠራተኛ እንደመሆንዋ መጠን እርዳታ የሚያስፈልገዉን አካባቢ በትክክል ለመለየት የሚረዱ መረጃዎችን መሰብሰብም አለባት።የበጎ አገልግሎት ተልዕኮዋን ስትጀምር ሥለመረጃ አሠባሰብ ግልፅ የሆነ ነገር አልነበረም።ሐሳቡን ራስዋ አፈለቀችዉ።

«እና ጥሩ ነገር ለማድረግ የምችለዉን ሞከርኩ።ከዚያም ይሕን ነፃነቴን ሙከራ አደረግሁበት።በቃለ መጠይቅ ላይ በተመሠረተ ሥልት ሠራሁበትና ምን ሊደረግ እንደሚችል አጤንኩኝ።በዚሕ መንገድ ከሥሕተቴ ተማርኩኝ።»

Deutschland Indien KfW Bewässerung in Indien

ሕንድ-የጀርመን የልማት ርዳታ

የራምቴኩ የሕንድ ቤተ-መቅደስ።ከመንደሪቱ በመኪና ሰወሰዓት ያሕል ያጉዛል።ለዶሪን ቤተ-መቅደሱን መጎብኘት በየመንደሮቹ ከምታደርገዉ የዘወትር ሥራዋ ለየት ያለ፥ አልፎ-አልፎ የምትከዉነዉ ነዉ።እዚያ ስትደርስ እንደ ሁሉም ጎብኚ ደዎሉን ደዉላለች።ከዚያ ከሕንዲዉ ቄስ ፊት ለፊት ስትደርስ እጆችዋን አጣጥፋ ተንበረከከች።ያቺ ወርቃማ-ፀጉር ነጭ ወጣት ያላደገችበን፥ ባሕል-አለሟ-ያልሆነዉን አለም ተቀየጠች።
Mark,kleber
ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic