የጀርመን ው, ጉ,ሚንስትርና የስለላውን ድርጅት የሚቆጣጠረው ኮሚቴ፣ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 18.12.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን ው, ጉ,ሚንስትርና የስለላውን ድርጅት የሚቆጣጠረው ኮሚቴ፣

የአሁኑ የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትርና በመራኄ-መንግሥት ሽሮኧደር የአስተዳደር ዘመን፣ የመራኄ-መንግሥቱ ጽ/ቤት ኀላፊ ነበሩ።

default

የጀርመን ው ጉ ሚ ፍራንክ ቫልተር እሽታይንማዬር፣የአገሪቱን የስለላ ድርጅት ተግባር ከሚቆጣጠረው የፓርላማ ኪሚቴ ፊት ቀርበው ለጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ፣

በዚህ ሥልጣናቸውም ፣ በፖለቲካው መስክ፣ የአገሪቱ የሥለላ ድርጅት ተግባር አስተባባሪ እንደነበሩ ይታወቃል። በጸረ-አሸባሪነት ዘመቻና በኢራቁ ጦርነት ወቅት፣ የጀርመን የስለላ ድርጅት፣ ያኔ ምን ዓይነት ድርሻ እንደነበረው ለማጣራት፣ ፓርላማው የሰየመው አጣሪ ኮሚቴ፣ ከሚያዝያ ወር፣ 1998 ዓ ም አንስቶ ሲጥር ቆይቷል። ኮሚቴው፣ ዛሬ፣ በመሥካሪነት ቃላቸውን ይሰጡ ዘንድ እሽታይንማየርን፣ ለ 5ኛ ጊዜ ያነጋግራል።----ተክሌ የኋላ---

የጌርሃርት ሽሮኧደር የሶሺያል ዴሞክራቶችና የያኔው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፣ የዮካ ፊሸር የአረንጓዴው ፓርቲ ጥምር መንግሥት፣ በኢራቁ የውጊያ ወቅት፣ ፀረ ጦርነት መሆኑን በተደጋጋሚ ሲለፍፍ እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን፣ አሁን አጣሪው ኮሚታ በተደጋጋሚ የሚያቀርበው ጥያቄ ፣ መንግሥት፣ በእርግጥ ያኔ የገለጠው ይፋ አቋሙ የቱን ያህል ተዓማኒነት ነበረው? የሚል ነው።

የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት (Bundestag ) ያቋቋመው መርማሪ ኮሚቴ፣ እ ጎ አ ታኅሳስ 14 ቀን 2006 ዓ ም ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፍርንክ ቫልተር እሽታይንማየርን የጠየቃቸው፣ በትውልድ ሊባኖሳዊ፣ በዜግነት ጀርመናዊ የሆኑትን ኻሌድ ኧል ማስሪን፣ የአሜሪካው ማእከላዊ የስለላ ድርጅት (CIA)እ ጎ አ በ 2003 ዓ ም ማለቂያ ላይ አፍኖ ወደ አፍጋኒስታን ሲወስደው ፣ ጉዳዩ የሚመለከተው የጀርመን ክፍል አያውቀም ነበረ ወይ? አፈጋኒስታን ውስጥ እሥር ቤት በተወረወረበት ድርጊት ፣ የጀርመን የስለላ ድርጅት ተሳትፏል ወይ? ለሚሉት ጥያቄዎች እሽታይንማየር ያኔ መልስ ሰጥተዋል። በኧል ማስሪ ጉዳይ በፍጹም አልነበርነበትም፣ ያሉት እሽታይንማየር ራሷ ጀርመን፣ የአሸባሪዎች አደጋ አንዣብቦባት ስለነበረ፣ ትኩረታችንን ሁሉ በዚያ ላይ ነበረ ያደረግነው ሲሉ ሶሺያል ዴሞክራቱ ፖለቲከኛ አስረድተዋል።

«በዚያ ወቅት፣ አንዳንዴ፣ ከባድ ውሳኔዎችን ማሳለፍ ተገቢ ነበር። ነገር ግን አረጋግጥላችኋለሁ ፣ ውሳኔዎቹ ተፈላጊ ቢሆኑም፣ ምንጊዜም፣ በህጉ መሠረትና፣ ጫፍ ድረስ የህጉን አንቀጽ እስከመጨረሻው በመተርጎም ነው የተሠራው። ይህ ድሮ ይሠራበት የነበረ ደንብ ነው። ወደፊትም ቢሆን በዚህ መንገድ እንደሚቀጥል አረጋግጥላችኋለሁ።»

ኧል ማስሪ እንዴት ታፍኖ ተወሰደ፣ እንዴት ከአፍጋኒስታን ወደ ጀርመን እንዲመለስ ተደረገ? መረማሪው ኮሚቴ ጥረት አድርጎ ምሥጢሩን ሊያገኘው አልቻለም።

በብሬመን ተወልዶ ያደገውና፣ መሰከረም 1 ቀን 1994 ዓ ም በኒው ዮርክ አሸባሪዎች ብርቱ ጥፋት ካደረሱ ከጥቂት ወራት በኋላ በሁዋንታናሞ ታሥሮ የነበረው ቱርካዊው ጀርመናዊ ሙራት ኩርናዝ ጉዳይም እንቆቅልሽ አንደሆነ ነው የቀረው። ከኒው ዮርኩ አደጋ በኋላ በዐመቱ፣ የመራኄ-መንግሥት ሸሮኧደር ጽ/ቤት ኀላፊ የነበሩት ያሁኑ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር እሽታይንማየር ኩርናዝ ባስቸኳይ ወደ ጀርመን እንዳይመለስ ሲሉ የተናገሩ ሲሆን፣ እ ጎ አ በመጋቢት 2007 ዓ ም፣ ለዚሁ የጀርመንን የስለላ ድርጅት ተግባር ለሚመረምረው የፓርላማ ኮሚቴ፣ ያንኑ ቃላቸውን ነው የደገሙት።

«እኔም ሆንኩ ማንም አቶ ኩርናዝ በሁዋንታናሞ መሠቃየታቸውን የሚጠራጠር የለም። ስለሆነም፣ ህጋዊ አያያዝ እንዲኖር የተቻለንን ሁሉ ጥረት አድርገናል። ጎን ለጎን ልትገነዘቡልን የሚገባ ጉዳይ፣ እኛ ም ለራሳችን ሀገር ፀጥታ ጥረት ስናደርግ እንደነበረ ነው።»

በኒው ዮርክ አንደኛውን የዓለም የንግድ ማእከል መንትያ ህንጻ በህዝብ ማመላለሻ አኤሮፕላን ከደረመሱት አብርሪዎች አንዱ ሙሐመድ አታ በሃምበርግ ይኖሩ ከነበሩት የአሸባሪ ቡድን አባላት አንዱ እንደነበረ ይታወቃል። ግራም

ግራም ነፈሰ ቀኝ ፣ ው ጉ ሚ እሽታይንማየር በግልም ሆን በፖለቲካ እስካሁን ስማቸውን የሚያጎድፍ ሁኔታ አልደረሰባቸውም።

የአረንጓዴው ፓርቲ ፖለቲከኛ Hans Christian Ströbele ግን እሽታይንማየርን እንዲህ ሲሉ ይዘልፋሉ።

«በጦርነቱ ወቅት በጣም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎች ለ ዩ ኤስ አሜሪካ ማእከል እንዳይተላለፉ (እሽታይንማየር) በቂ በሆነ መልኩ ያደረጉት ጥረት የለም።»

Spiegel በተሰኘው የጀርመን መጽሔት የቀድሞው የአሜሪካ ጀኔራል ጄምስ ማርክስ ከ CIA ይልቅ ከጀርመን በኩል ያገኘነው መረጃ ይበልጥ የሚያስተማምን ነበረ ማለታቸው የሚታወስ ነው።

የአሁኑ የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትርና በመራኄ-መንግሥት ሽሮኧደር የአስተዳደር ዘመን፣ የመራኄ-መንግሥቱ ጽ/ቤት ኀላፊ ነበሩ። በዚህ ሥልጣናቸውም ፣ በፖለቲካው መስክ፣ የአገሪቱ የሥለላ ድርጅት ተግባር አስተባባሪ እንደነበሩ ይታወቃል። በጸረ-አሸባሪነት ዘመቻና በኢራቁ ጦርነት ወቅት፣ የጀርመን የስለላ ድርጅት፣ ያኔ ምን ዓይነት ድርሻ እንደነበረው ለማጣራት፣ ፓርላማው የሰየመው አጣሪ ኮሚቴ፣ ከሚያዝያ ወር፣ 1998 ዓ ም አንስቶ ሲጥር ቆይቷል። ኮሚቴው፣ ዛሬ፣ በመሥካሪነት ቃላቸውን ይሰጡ ዘንድ እሽታይንማየርን፣ ለ 5ኛ ጊዜ ያነጋግራል።----ተክሌ የኋላ---