የጀርመን ውህደት 25ኛ ዓመት መታሰቢያ | ዓለም | DW | 03.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የጀርመን ውህደት 25ኛ ዓመት መታሰቢያ

ካፒታሊስት ምዕራብ ጀርመንና ሶሻሊስት ምስራቅ ጀርመን የተዋሃዱበት 25ኛ አመት ተከበረ። በበርሊን ግንብ መናድ የተጀመረው ውህደት አስፈላጊ ቅድመ-ሁኔታዎች ተሟልተው የተጠናቀቀው በመስከረም 23 ቀን 1983 ዓ.ም. ነበር።

ምዕራብ እና ምስራቅ ጀርመን የተዋኃዱበት 25ኛ ዓመት ዛሬ ተከብሮ ዋለ። በፍራንክፈርት ከተማ በተዘጋጀው በዚሁ ክብረ- በዓል ላይ የጀርመን ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል። 1500 እንግዶች በተጋበዙበት ክብረ- በዓል ላይ ንግግር ያደረጉት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ዮሀይም ጋውክ « ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጀርመናውያን በተዋኃደችው ጀርመን ቤተኝነት ይሰማቸዋል፤ ጀርመን በነፃነት አንድነትን ላይ ደርሳለች ብለዋል። ጋውክ፤ ወቅታዊውን የስደተኞች ቀውስም በንግግራቸው ላይ በማንሳት ጉዳዩ የአውሮፓ የጋራ ርምጃ እንደሚሻ አስታውሰዋል። በፍራንክፈርት ኦፔራ ከተዘጋጀው የግብዣ ስነ ስራዓት በፊት ፤መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል፤ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ክርትያን ቩልፍ እና ሌሎችም ባለስልጣናት ፍራንክፈርት የሚገኘው የዶም ቤተ ክርስትያን በተዘጋጀው የፀሎት ስነ ስርዓት ላይ ተካፍለዋል።

ልደት አበበ

እሸቴ በቀለ