የጀርመን እገዛ ኢትዮጵያውያን ተመላሾች | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 30.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን እገዛ ኢትዮጵያውያን ተመላሾች

የጀርመን አለም አቀፍ የፍልሰትና የልማት ማዕከል እጎአ ከ2004 አመተ ምህረት አንስቶ በፍላጎታቸው ወደ ሃገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጰያውያንን በማገዝ ላይ ይገኛል ።

ማዕከሉ በተለይ እውቀትና የሥራ ልምድ ያካበቱ ምሁራን ወደ ሃገራቸው ተመልሰው በሚፈለጉባቸው የሥራ መስኮች እንዲያገለግሉ ማድረግ ዋናው ትኩረቱ ነው ። ከጀርመን ወደ ኢትዮጵያ በፍላጎታቸው ለሚመለሱ ኢትጵያውያን ምሁራን እገዛ የሚያደርገው የጀርመን አለም አቀፍ የፍልሰትና የልማት ማዕከል የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ። ማዕከሉ ስለ ሚያከናውናቸው ተግባራት የኢትዮጵያው ቅርንጫፍ የፍልሰትና የዳይስፖራ መርሃ ግብር ሃላፊ ወይዘሮ ኮከቤ ኃይለ ገብርኤል

የጀርመን አለም አቀፍ የፍልሰትና የልማት ድርጅት በምህፃሩ CIM የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ የፍልሰትና የዳይስፖራ መርሃ ግብር ሃላፊ ወይዘሮ ኮከቤ ኃይለ ገብርኤል መስሪያ ቤታቸው ለነማን እገዛ እንደሚያደርግ የተናገሩት ። የጀርመን አለም አቀፍ የፍልሰትና የልማት ማዕከል እጎአ ከ2004 አመተ ምህረት አንስቶ በፍላጎታቸው ወደ ሃገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጰያውያንን በማገዝ ላይ ይገኛል ። ማዕከሉ በተለይ እውቀትና የሥራ ልምድ ያካበቱ ምሁራን ወደ ሃገራቸው ተመልሰው በሚፈለጉባቸው የሥራ መስኮች እንዲያገለግሉ ማድረግ ዋናው ትኩረቱ ነው ። በጀርመን አለም አቀፍ የትብብር መስሪያ ቤት በምህፃሩ ጂ.አይ.ዜድ እንዲሁም ከፌደራል ጀርመን የጀርመን የስራ ቅጥር ጉዳይ መስሪያ ቤት በትብብር ሥራውን የሚያካሂደው ይህ ማዕከል በተለይ ትኩረት የሚሰጣቸው የሙያ መስኮች አሉ ።

P1010173 Wolkite Solar-Center Reparatur Ladekontroller : bt Copyright: Stiftung Solarenergie, Fotograf: York Ditfurth Uneingeschränktes Verwertungsrecht für die Deutsche Welle Weitere Stichwörter für die Suche (bitte eingeben): Solar Solarenergie PV Äthiopien Sonnenenergie ländliche Elektrifizierung Kerosien LED

ወይዘሮ ኮከቤ እንደሚሉት ጀርመን አገር የተማረም ሆነ የሰራ ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ተፈላጊ ነው ። በማዕከሉ የሚረዱት ግን መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ናቸው ።

በኢትዮጵያ ምሁራን የሚፈለጉባቸው የተለያዩ የስራ መስኮች አሉ ። ሆኖም እንደ ወይዘሮ ኮከቤ ምሁራን በብዛት የሚፈለጉባቸው የሙያ መስኮች በየአመቱ ሊለያዩ ይችላሉ ።

እንደ ወይዘሮ ኮከቤ አሁን ደግሞ በብዛት የሚፈለጉት የስራ አመራር እውቀትና ልምዱ ያላቸው ባለሞያዎች ናቸው ሆኖም ከጀርመን የተመለሱ ምሁራን በሙሉ እንደሚፈለጉት ወይም የሚጠበቁትን ያህል ሆነው ላይገኙም ይችላሉ ።

የጀርመን አለም አቀፍ የፍልሰትና የልማት ድርጅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በ18 አገራት ተመሳሳይ ተግባር ያከናውናል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic